Tag Archives: meles zenawi

የአገር ቤት ጋዜጦች ምን ጻፉ?

የበርማ ጄነራሎች እንኳ ሳንሱኪን ያሰሩበት ኹኔታ ከብርቱካን ጋር አይነጻጸርም፡፡ የብርቱካን የከፋ ነው፡፡ የእኛ መሪ ተብዬዎች የበርማ ጄኔራሎችን ያህል እንኳ ሆደ ሰፊነት የላቸውም፡፡ ለስድስት ወራት ያህል ሰው በማይታይበት፣ መፀዳጃ ባልነበረበት አደገኛ ቦታ አስረው ሥነልቡናዋን ለመስበር ሞክረዋል፡፡ እስር ቤቱን አውቀዋለሁ፡፡ ታስሬበት ነበር፡፡ የእርሷ ግን እኔ ከማውቀው እጅግ የከፋ፣ ከበርማ ጄኔራሎች ሁሉ እጅግ የከፋ፣ እኩይ ሥነ-ምግባር በተጠናወታቸው ሰዎች የተወሰደባት ርምጃ ነው፡፡ ሰማይ እንኳ እንዳታይ መስኮት ያልነበረው ክፍል ውስጥ ነው መጀመርያ ላይ ያሰሯት፡፡

Read more
Abaaduula2

አቶ አባዱላ ገመዳ አፈጉባኤ፣ መለስ ዜናዊ ጠ/ሚኒስትር ወ/ሮ ሽታዬ ም/አፈ ጉባኤ ኾነው ተመረጡ

በተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛው የሥራ ዘመን የመጀመርያ ጉባዔ አዲስ መንግሥት እየተመሠረተ ነው። በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዬርጊስ ንግግር የተከፈተው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስብሰባ አቶ ደግፌ ቡላን ተክተው እንዲሠሩ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃንን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧቸዋል። አቶ ካሳ በትጥቅ ትግል ተሳትፎ የነበራቸው ነባር የብአዴን የሥራ አስፈፃሚ አባልነት ሲኾን [...]

Read more