በግዳጅ ማፈናቀል ለ “አዲስ ድህነት”
የሸራተን አካባቢ እና ሌሎች በልማት ስም ተፈናቃይ ኢትዮጵያውያን እንደ ሜክሲኮ ገበሬዎች የመደራደር አቅም የላቸውም። እንኳን በእገታ እና በነውጥ መንግሥትን ሊያስገድዱ ቀርቶ መብታቸውን እንኳ ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ለእስር የመዳረግ ዕጣን አከናንቧቸዋል። የመግሥትን የልብ ትርታ ያዳመጠ በሚመስል መንገድ “ልማታዊ ነን” ብለው ቢማጸኑም መንግሥት እውቅና ያልሰጠው ልማታዊ ሰው/ቡድን/ሕዝብ “ፀረ ልማት” ነው ተብሎ በሚፈረጅበት አገር ስላሉ “ጸረ ልማት” እና “አመጽ ቀስቃሽ” ናችኹ በሚል ክስ ለእስር ተዳርገዋል። ሌሎቹም ጥያቄያቸውን ደግመው እንዳያነሱ ጎረቤቶቻቸውን መቀጣጫ ስላደረጉባቸው ታፍነዋል። 5ሺሕ የሚኾኑት አባወራዎች “የአዲሱ ድህነት” መሞከሪያዎች ኾነዋል።
Read more
3 November 2010 