Addis Neger » Religion

ያልተዳሰሱ የሐውልቱ ወጎች
መንበረ ፓትርያርኩን ከያዙ አንስቶ አንድም ጊዜ ከማወዛገብ አርፈው የማያውቁት አቡነ ጳውሎስ በ18ኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸውም ላይ ከወትሮው የተለየ ነገር ግን ሌላ ውዝግብን መርቀው ከፍተዋል። የሐሳቡ አመንጪ እሳቸው ባይኾኑም ለሰሞኑ እሰጥ አገባ ምክንያት የኾነውን “የመታሰቢያ ሐውልት” መርቀው በመግለጣቸው ምክንያት የራሳቸውን ሐውልት እንዳቆሙ ተቆጥሮ ትችት በዝቶባቸዋል። በሺህ የሚቆጠሩ መጻሕፍቷ ከትህትና እና ውዳሴ ከንቱን ከመፍራት የተነሳ በማን እንደተጻፉ በማይታወቅባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ “እኔን አስቡኝ፣ ታላቅነቴን ተቀበሉ” እንዳሉ ተቆጥሮ ሕዝበ ክርስቲያኑን “እግዚኦ ምን አይነት ዘመን ላይ ደረስን!” አሰኝተዋል። በምርቃቱ ላይ የታደመው ቁጥሩ ቀላል የማይባለው ሰው ትንግርት የኾነበትን ይህን ሐውልት ፓትርያርኩ መርቀው ሲከፍቱ ሌላም ዐይን የሚገባ ትእይንት በሐውልቱ ሥር ይመለከት ነበር። ይህን ሐውልት በማሰራት እርሳቸውን ለማስደሰት ደፋ ቀና ያሉት የሴት እና የወንድ አጃቢዎቻቸው ለአዲሱ ሐውልት ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያወቁት አይመስልም። እንደመስገድም የ ”ቡራኬዎ ይድረሰን” አድንኖም የሚመስል እንቅስቃሴ ሲያደርጉም ታይተዋል።

ቀራጺው አቶ ብዙነህ ተስፋ ሐውልቱን እንዲሠራ ሲነገረው የተሰማው ደስታ ልክ አልነበረውም። ሐውልቱ የሚሠራላቸው ግለሰብ በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ስምም ይኹን ሐውልቱ ሊያመጣው የሚችለው ውዝግብ ለእርሱ አልተከሰተለትም። “ሰውየውን በጣም ነው የማደንቃቸው” የሚለው አቶ ብዙነህ የእኚህ ሰው የተማረ ሰብእናና በእርሱ አገላለጽ “ማቹርድ አስተሳሰብ” ይማርከዋል። “ከዚህ በፊትም የድምፃዊውን የጥላሁን ገሰሰን ሐውልት ሰርቻለኹ” ይላል ብዙነህ ያንን ሐውልት ለመሥራት በነበረው ውድድር ላይ በማሸነፉ የተሰማውን ደስታ በኩራት እያስታወሰ። “በጥላሁን ሐውልት ውድድር ላይ መምህራኔን ሳይቀር ነው ያሸነፍኩት!”ይላል። የሞያ ብቃቱንም ለማሳየት ይሟገታል “የታዋቂ ሰዎችን ሐውልት መሥራት እኮ ቀላል ነገር አይደለም!”

ሌሎች የሙያ ባልደረቦቹ በዚህ የብዙነህ ሥራ ላይ ያላቸው አመለካከት የተለየ ነው። የሥራውን ሥነ ጥበባዊ ዋጋ “mediocre standard” (ተራ) ሲሉ ይገልጹታል። በሃውልቱም ሞራላዊ አግባብነት ላይ እንዲሁ ጥያቄአቸውን ማንሳታቸው አልቀረም። አቶ ብዙነህ የሚያደንቃቸው ግለሰብ ሃውልት መቆሙ አግባብነቱ አያጠራጥረውም። እንዲያውም ሃውልት ሊቆምባቸው የሚቻሉ ዝርዝር ምክንያቶችን እየገለጸ ለማሳመን ጥረት ያደርጋል። የግለሰቡም ስብእና ሃውልት ሊቆምለት የሚገባው እንደኾነ ይከራከራል “የእኛ ሰው ሰውን ካልሞተ በቀር አያመሰግንም” ይላል። አንድ ቀን ግን የሰውየውም ማንነት ኾነ የእርሱ ሥራ የሚመሰገንበት ዘመን እንደሚመጣ እርግጠኛ ነው።

ከመዋቲነት ጋራ ትግል

የቅርጻ ቅርጽ ባለሞያዎቹ የሰው ልጅ የራሱ ምሥል በሐውልት መልክ እንዲቆምለት የሚፈልግበትን ሥነ ልቡናዊ ምክንያት ሲያስረዱ “የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ከኾነው ሞት ጋራ ኹሌም እንደታገለ ይኖራል” ይላሉ። እንደ ባለሞያዎቹ ገለጻ ሞትን ሊያሸንፍ ከሚሞክርባቸው ነገሮች አንዱ ሐውልትን በመሰሉ ቋሚ ነገሮች ምሥሉን ትቶ ማለፍ ነው። አዲስ ነገር ያነጋገረቻቸው ባለሞያዎች የፓትርያርኩን ሐውልት አስመልክቶ ግርምትን የሚፈጥርባቸው ጉዳይም ይህ ነው። “ለምድራዊ ነገር ሞቻለኹ የሚል እና የዚህን ዓለም ከንቱነት የሚያስተምር ተከታዮቹንም በሚመጣው ዓለም ተስፋ እንዲያደርጉ የሚሰብክ ሰው ይህን ማድረጉ” ለእነርሱ ከሐውልቱ ወጎች ሁሉ የላቀው ግርምት ነው። የሐውልቱ ባለቤት ይኹንታ ታክሎበት ይህ ሐውልት መቆሙንም “የደረስንበትን የሞራል ውድቀት” የሚያሳይ ምስክር አድርገው ይገልጹታል።

ገና ሐውልቱ ሳይቆም ጀምሮ “አግባብ ነው አግባብ አይደለም” የሚለው ክርክር ጎራ ከፍሎ ሲያወዛግብ ቆይቷል። የክርክሩ አካሄድ ሚዛኑ ወዴትም ያጋድል አያጋድል ያላስጨነቃቸው የሐሳቡ አፍላቂዎች ሐውልቱን ከማቆም ያገዳቸው አንዳች ነገር አልነበረም። ሐውልቱም በዐይነቱ የመጀመሪያ የኾነ ሥነ ሥርዐት ተደርጎ እና በራሳቸው በፓርትያርኩ ተመርቆ ተገልጦ ብዙ ሕዝብ በተገኘበት ይፋ ኾኗል። ስለዚህም አከራካሪ ሐውልት እጅግ ብዙ አስደናቂ ዜናዎች ተሰምተዋል። “በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶበታል፣ ለአምስት መቶ ዓመት የሚቆይ ዕድሜ አለው፣ አፈር ውስጥም ቢቀበር አይበሰብስም… ” አንዳንዱ ዘገባ የሐውልቱን ሥራ የተቃወሙትን ሰዎች ለማናደድ ኾን ብሎ የተነገረም መስሏል;፡

የምን አምስት መቶ ዓመት?

የሐውልቱን አሠራር የተመለከቱት ባለሞያዎች የሚባለውን ያህል ገንዘብ እንዳላወጣ ግምታቸውን ሲሰጡ ቢቆዩም፤ በሰፊው ሲወራ የነበረው የሐውልቱ ዋጋ 300.000 የአሜሪካን ዶላር (ወደ አራት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ) እንደኾነ ነበር። የፓትርያርኩን  ሞገስ ለማግኘት ሲሉ በቅርባቸው ያሉ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች እንዳሠሩት የሚነገረው ይኸው ሐውልት ለ18ኛ ዓመት በዐለ ሲመታቸው የተበረከተ የእጅ መንሻ እንደኾነ ሲነገር ከርሟል። ለዚህ ጽሑፍ ዝግጅት አዲስ ነገር ያነጋገረችው የሐውልቱ ቀራጺ ብዙነህ ተስፋም ሐውልቱ ይህን ያህል እንዳላወጣ ገልጿል። “ሐውልቱ ያወጣው ሁለት መቶ ሺሕ የኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው” ሲል ገልጿል አቶ ብዙነህ።

የሐውልቱንም ዕድሜ በተመለከተ ሲነገር የነበረውን አምስት መቶ ዓመት አቶ ብዙነህ አያውቀውም። “እኔ እንዲህ ዐይነት ዋስትና አልሰጥም” ሲል ጫን ባለ አነጋገር የሐውልቱ ዕድሜ ያን ያህል ሊኾን አንደማይችል አስቀምጧል። ከዚህ በተጨማሪ ሐውልቱ የተሠራው ከናስ ነው የሚለውንም አስተያየት ያስተባብላል፤ ሐውልቱ የተሠራው ፋይበር ግላስ ከተባለ ግብአት ነው በማለት። ከዚህ ዐይነቱ ቁስ የሚሠራው ሐውልት ደግሞ ዕድሜው ከስድሳ እና ከሰባ አይበልጥም የሚለውን ግምቱንም ያስቀምጣል። አቶ ብዙነህ በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በኢየሩሳሌም ተመሳሳይ ሐውልቶች ይሠራሉ ስለሚባለው መረጃ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ይህም ጉዳይ ለበዙነህ “እንዲሁ በወሬ ደረጃ የተነገረ ጉዳይ” ተብሎ የሚታለፍ ነው።

በቀራጺው አመለካካት እና ዕይታ “ሕዝቡ አመነበትም አላመነበትም ሐውልቱ ለፓትርያርኩ ይገባቸዋል።” በዚሁ መለኪያው ከሐውልቱ ጋራ ተያይዘው ለሚነሱት ጥያቄዎች ቦታ እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም። መከራከርያው ምን ያህል እንደሚያስጉዘው ያሰበበት በማይመስል አኳኋን “አብዛኛው” ሕዝብ የሐውልቱን አግባብነት ባይቀበለው ለእርሱ ግድ አይሰጠውም። “እዚያ ቦታ ላይ ቆሻሻ ቢደፋበት ኖሮ የሚናገር አንድ ሰው አይገኝም።” ሲል መሟገት ይፈልጋል። ይህንኑም በጥያቄ መልክ ሲያቀርብ እንዲህ ይላል “ከቆሻሻ እና ከሐውልቱ ቆሻሻው ለምን እንደተመረጠ አልተከሰተልኝም?”

አቶ ብዙነህ ይ ለህን ለመሳሰለው ጉዳይ መፍትሄ ለማምጣት እንዲሁም ከአማኙ ሊመጣ የሚችለውን ጥያቄ ከመጀመርያው ለማስቀረት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ይገልጻል። ከስድስት እስከ ሰባት ሜትር የሚደርስ ሐውልት በቦታው ላይ መሥራት ሲቻል፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኑን ከለለው የሚል ስሞታ እና ትችት እንዳይፈጠር “ሐውልቱ ከቤተ ክርስቲያኑ አጥር መብለጥ የለበትም” የሚለውን ሐሳብ ያቀረበው እርሱ መኾኑን ይናገራል። ይህም ሐውልቱን ዐይን የማይገባ እንዲኾን እንዳደረገው ያስባል።

ለሌሎቹ ቀራጽያን የሐውልቱ ዐይን አለመግባት ምክንያቱ ቁመቱ በሰው ቁመት ልክ (life size) ኾኖ መገኘቱ እና የቦታ አመራረጥ ችግር ነው። “የሐውልቱ ደካማ አሠራር (composition) ከተተከለበት የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሰፊ እና ክፍት ቦታ አንጻር የማይመጥን ነው።” ይላሉ አንዱ ባለሞያ፤ ይህም ሐውልቱን “ክርስቶስን በምድር የሚወክል ባለ ግርማ ሰው ምሥል ከመኾን ይልቅ አጭር (dwarf) የሰው ቅርጽ” እንዲመስል አድርጎታል። ይህም እንደ ባለሞያው ገለጻ ሐውልቱ የቆመበት ሥፍራ “በድንገት የተመረጠ” እንደኾነ የሚያሳይ ነው። ይህ ራሱ ሐውልቱን የተከበረ ሰው መታሰቢያ ከመኾን ይልቅ “ክብር የሌለው ብረት ኾኖ ለረጅም ጊዜ እንዲቆም ያደርገዋል” የቁመቱን ማጠር ሐሳብ እርሱ እንዳቀረበው የማይክደው ቀራጺው አቶ ብዙነህ ግን ቁመቱ በሰው ቁመት ልክ አለመኾኑን ለማሳመን ጥረት ያደርጋል። “የፓትርያርኩ ቁመት አንድ ሜትር ከ71 ሳንቲ ሜትር ነው። ሐውልቱ ግን ከመቆምያው ውጪ ሁለት ሜትር በመኾኑ ከፓትርያርኩ  ቁመት በ29 ሳንቲ ሜትር ይበልጣል።” ይላል።

የንጉሡ ሐውልት ደካማ ቅጂ?

ባለሞያዎቹ ከሚያነሷቸው የሐውልቱ ደካማ ጎኖች አንዱ እነርሱ (pedestal) የሚሉት የሐውልቱ መቆሚያ ነው። ይህ የሐውልቱ መቆሚያ ጅማ የነበረው የቀዳማዊ ኀይለሥላሴ ሐውልት እስከ አብዮቱ መምጣት ድረስ ቆሞበት የነበረው ፔድስታል ቅጂ ነው። “ከሌላ ሰው ሥራ አንዳንድ ነገሮችን መውሰድ ስህተት የለበትም” የሚሉት አንድ ባለሞያ የመጀመርያውን ሥራ የሠራው ሰው ለምን ያንን ዐይነት ሥራ እንደመረጠ ማጥናትን ይጠይቃል። “የመጀመሪያው ቀራጺ ያለምክንያት እንዲህ ዐይነት መቆሚያ ሊሠራ አልፈለገም” ይላሉ። እርሱ ያንን የመረጠበት ነባራዊ ኹኔታም የመድኃኔዓለም አካባቢን የሚመለከት ላይኾን ይችላል። በመኾኑም ይህ የሐውልቱ ክፍል የንጉሡ ሐውልት ደካማ ቅጂ ነው። በመኾኑም ቀራጺው “የመጠን፣ የቀለም እና የሚሠራበት ግብአት (material) ሳያጠና ያለ አግባብ የተደረገ” ቅጂ ነው። በመኾኑም ይህ ቅጂውን ደካማ እንደሚያስብለው ይናገራሉ።

ቀራጺው አቶ ብዙነህ ያንን የቀድሞ የጅማ ሐውልት እንደማያውቀው ይናገራል። “የእኔው የራሴ ዲዛይን ነው።” ሲልም ያረጋግጣል። “ሐውልቱ እንዲሁ ዝግ እንዳይኾን በማሰብ ቅለተን (transparency) ለመፍጠር በማሰብ የፈጠርኩት ዲዛይን ነው” ይላል አቶ ብዙነህ። “የንጉሡን ሐውልት ዲዛይን አላውቀውም” የሚለው የአቶ ብዙነህ ሐሳብ አልዋጥልህ ያላቸው ባለሞያ “በእንደዚህ ዐይነት ሥራ ወቅት ከዚህ ቀደም የተሠሩ ሥራዎችን በማየት የማነጻጸር ግዴታም ቢኾን የራሱ የቀራጺው” ነው ሲሉ ይተቻሉ። በዚህም ሥራ ላይ “ቀጥተኛ የዲዛይን መመሳሰል” መኖሩ አያጠራጥራቸውም።

ምን ዐይነት ስሜት በሕዝብ ላይ እንደሚያሳድር ያልተጨነቁለት የሚመስለው የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት ዐይነ ግቡዕ በኾነው የከተማዋ ክፍል ቆሟል። የሐውልቱ መቆም አግባብነት ያልተፈታ ቢኾንም ሐውልቱ ያለውም የውበት (esthetic) ዋጋ እንደያዚያው የሚያነጋግር ኾኗል። የቅርጻ ቅርጽ ባለሞያዎቹ እንዲህ ዐይነት የአደባባይ ምሥሎች ሕዝቡ በግለሰቡ ላይ ያለውን አመለካከት ለማስቀየር እና ክብር ለማግኘት ታስበው የተሠሩ ከኾነ ውጤታማነታቸው አጠራጣሪ መኾኑን ይናገራሉ። “የሌኒን ሐውልት እኮ የሩቅ ጊዜ ትዝታ አይደለም” ይላሉ። ያም ሁሉ ኾኖ ይህን ሁሉ ክርክር ያልሰማው የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት የማይፈልጉትንም የሚፈልጉትንም ሊባርክ ቀኝ እጁን ዘርግቷል።