Archive | Arts & Culture RSS feed for this section
IMG_94081

Aster Aweke Releases New Album Today

Aster Aweke’s 23rd  album, “Checheho”, is to be released today, December 25, 2010. The album is named after a small town in Gonder, the region where Aster where born. The Ethiopian diva released a new single, “Checheho”, a month prior to the launch of the album, which contains 13 other songs. The album was recorded [...]

Read more
ramatohara cover 1

የአገር ወይስ የሥነ ጽሑፍ ፍቅር?

ይስማእከ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የሚጠቅሳቸው እና “የሥነ ጽሑፍ ስብራቱን” በ “ወጌሻ ምክራቸው” እንደጠገኑለት የሚያወድሳቸው “መካሪዎቹ” ያላዩዋቸው የሚመስሉ እጅግ ብዙ፣ ብዙ “ስብራቶች” በመጽሐፉ ውስጥ በጉልህ ይስተዋላሉ። የይስማእከ በእድሜ ወጣት ከመኾኑ የተነሳ እንደ ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድኅን አባባል “በሳርም፣ ባሳርም” ተምሮ ያልጨረሳቸው ብዙ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግልጽ ነው። (በድፍረት የሠራቸው ብዙ ስህተቶች እንዳሉ ባይዘነጋም) በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ስማቸውን ያነሳቸው የሥነ ጽሑፍ ባለሞያዎች ግን እነኚህን የሚጎረብጡ ስህተቶች እንዴት ሊያልፏቸው እንደቻሉ ለብዙዎች ያስገርማቸዋል። በእርግጥ ይስማእከ እነዚህ ሰዎች በመጽሐፉ ላይ የነበራቸው አስተዋጽዖ እስከምን ድረስ እንደነበረ አይነግረንም። በመኾኑም እነዚህን ሰዎች እርሱ ስማቸውን ስለጠቀሰ ብቻ የስህተቱ አጋር አድርጎ ማሰብም አስቸጋሪ ሊኾን ይችላል። ይስማእከም የእነርሱን አስተያየት “ሙሉ በሙሉ” እንዳልተቀበለ በስልክ ውይይታችን ላይ ገልጿል። ምክንያትም አለው፤ “የራሴ የኾኑ ቀለሞች ከመጽሐፉ እንዲጠፉ አልፈለግሁም” የሚል።

Read more
Tedy and Dagmawi

ቴዲ አፍሮ በካምፓላ

ከአገሩ ከወጣ 20 ዓመት የኾነው አንድ ኢትዮጵያዊ “እኔ በአገሬ ላይ ቴዲን ለማየት ባልችል ወደ “አገሬ/ዩጋንዳ” ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህልኝ ብዬ ለመቀበል ነው የመጣኹት። ዛሬ ሁሉም ዘፈን ቀርቶብኝ አንድ ዘፈን እንዲዘፍንልኝ እፈልጋለሁ። በቅርቡ የለቀቀውን “አልሞላውም ኪሴን” የሚለውን። እሱን ካልዘፈነ እናደድበታለሁ።” አለ። በዚህ ዘፈኑ ቴዲ ሞራሊስት መኾኑን እንዳረጋገጠለት ይናገራል። “እንደ ማኅበረሰብ ከፍተኛ የኾነ የሞራል ልሽቀት ውስጥ መኾናችንን በደንብ እየሳየን ነው። ለገንዘብ ስንል ማንነታችንን ጥለናል። እሴቶቻችን ረስተናል። ስግብግብ እና ቀጣፊዎች፣ ሌቦች እና ቀማኞች ኾነናል። በዚሁ ማንነታችንም ደስታን አጥተናል። ይሉኝታ እና ኅሊና ቢስ ከመኾን ይልቅ ማጣትን እመርጣለሁ እያለ ነው።” ይለዋል ለሞራሊስትነቱ ምክንያት ሲደረድር።

Read more

ማሃሙድ ጋ ጠብቂኝ! [ክፍል አራት፤የመጨረሻ]

ፒያሳን የምወድበት ሌላው ምክንያት ባቅላባን ስላስተዋወቀችኝ ነው፡፡(አንዳንዶች ‹‹ቫቅላባ›› ነው የሚባለው ይላሉ፡፡ እኛ ምናገባን፣ ባቅላባውን እንጂ ሆሄያቱን አንበላቸው፡፡)…ይህ የፒያሳ ጭንቅላት ዛሬ ራስ ቅሉ ብቻ ነው ያለው፡፡ በውስጡም ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት የሆኑ እርኩሳን የኤንጂኦ መናፍስትን እያስጮኹ የሚያስወጡ የባህል መድኀኒት አዋቂዎች ተቀምጠውበታል፡፡ ብሪትሽ ካውንስል፣ ነፍስ ይማር!…ፒያሳ እንዲህ ያወጋሁህን ያህል ብቻ አይደለችም። ምኑን ነካሁትና?! ፒያሳ በሕይወት የተሞላች ብትሆንም ብዙ ሲባልላት ባለመስማትህ ግነ ተገርመህ ይሆናል። አትገረም። “ለእነ እንትና ተዘፍኖ ለፒያሳ ሳይዘፈን ይቅር?” ብለህም ይሆናል። አትቆጭ። ምክንያቱ ወዲህ ነው፤ ፒያሳን ለመግለጽ ቋንቋም ወኔ ይጎለዋል። ቋንቋን ራሱን በፒያሳ ሕይወት ተመስጦ ልታገኘው ትችላለህ። ፒያሳን ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ ፒያሳን መኖር የበለጠ ሐሴት ይሰጣል፤ የስጋም የነፍስም። ይሄው ስንት ዓመታችን ፒያሳን ስንኖራት። የፒያሳ ልጆች ፒያሳን አብረሃቸው እንድትኖር ጋብዘውሃል። ወደ ግብዣው ስትሄድ ግን እስካሁን የሰጠሁህን ምክር በልብህ ያዝ፤ አለበለዚያ የእንትን (የፈለከውን ሰፈርና ከተማ ስም እዚህ ጋ ማስገባት ትችላለህ) ልጅ ነው ብለው ይጥሉሃል። ፒያሳ፤ ማሃሙድ ጋ እንገናኝ!

Read more
Feleke and Meseret

የኢትዮጵያ “ኦስካር” ምሽት

የለቀቀውን መድረክ መልሶ የተረከበው ሰይፉ የዓመቱን ምርጥ ወንድ ተዋናይን ማንነት ለማሳወቅ እየተንደረደረ እያለ ከተመልካች መካከል “ግሩም” የሚል ጩኸት በአዳራሹ አስተጋባ። ገማቹ ተመልካች ትክክል ነበር። “ትዝታህ” እና “ይሉኝታ” በተሰኙ ሁለት ፊልሞች በመሪ ተዋናይነት የተጫወተው ግሩም በሁለቱም ምርጥ ተብሎ መመረጡን በመድረኩ አስተዋዋቂዎች በኩል ተገልጿል። ግሩም “ሄርሜላ” በተሰኘው የዮናስ ብርሃነ መዋ ፊልም በተመልካች ዘንድ እውቅናን ከማግኘቱ በፊት “መስዋዕት” በሚለው የቪዲዮ ፊልም ላይ በመተወን ሥራውን ጀምሯል። በአሁኑ ሰዓት ካሉት ወጣት ተዋንያን በብዙዎቹ ፊልሞች ላይ በመሳተፍ እና በትወናውም የዋና እና የረዳት ገጸ ባሕርያት በመወከል የተዋጣለት ተዋናይ እየኾነ ነው።

Read more