Archive by Author
ramatohara cover 1

የአገር ወይስ የሥነ ጽሑፍ ፍቅር?

ይስማእከ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የሚጠቅሳቸው እና “የሥነ ጽሑፍ ስብራቱን” በ “ወጌሻ ምክራቸው” እንደጠገኑለት የሚያወድሳቸው “መካሪዎቹ” ያላዩዋቸው የሚመስሉ እጅግ ብዙ፣ ብዙ “ስብራቶች” በመጽሐፉ ውስጥ በጉልህ ይስተዋላሉ። የይስማእከ በእድሜ ወጣት ከመኾኑ የተነሳ እንደ ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድኅን አባባል “በሳርም፣ ባሳርም” ተምሮ ያልጨረሳቸው ብዙ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግልጽ ነው። (በድፍረት የሠራቸው ብዙ ስህተቶች እንዳሉ ባይዘነጋም) በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ስማቸውን ያነሳቸው የሥነ ጽሑፍ ባለሞያዎች ግን እነኚህን የሚጎረብጡ ስህተቶች እንዴት ሊያልፏቸው እንደቻሉ ለብዙዎች ያስገርማቸዋል። በእርግጥ ይስማእከ እነዚህ ሰዎች በመጽሐፉ ላይ የነበራቸው አስተዋጽዖ እስከምን ድረስ እንደነበረ አይነግረንም። በመኾኑም እነዚህን ሰዎች እርሱ ስማቸውን ስለጠቀሰ ብቻ የስህተቱ አጋር አድርጎ ማሰብም አስቸጋሪ ሊኾን ይችላል። ይስማእከም የእነርሱን አስተያየት “ሙሉ በሙሉ” እንዳልተቀበለ በስልክ ውይይታችን ላይ ገልጿል። ምክንያትም አለው፤ “የራሴ የኾኑ ቀለሞች ከመጽሐፉ እንዲጠፉ አልፈለግሁም” የሚል።

Read more
abba

የአክሊሉ ሀብተወልድ ታሪክ ሌላ የኀዘን ትዝታ

የመጽሐፉ 92 ገጾች ጠቅላይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሀብተወልድ ከልጅነታቸው ዘመን የትምህርት ቤት ታሪክ አንስቶ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኾነው እስከተሾሙበት የአጼ ኀይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ማብቂያ ድረስ ያለውን የሥራ ዘመናቸውን ታሪክ ይተርካል። አሳታሚው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ለዚሁ የአክሊሉ ሀብተወልድ መጽሐፍ የእንግሊዘኛ ትርጉም እንዲኖረው እና አብሮ እንዲጠረዝ አድርጓል። ከአማርኛው ሥራ በተለየም እንግሊዘኛው ብዙ ጠቃሚ የኾኑ ነገሮችን አካቷል። ጸሐፊው ከመገደላቸው በፊት እንደተናገሩት አቶ ከተማ ይፍሩ ያስታወሱት አባባል፣ የተርጓሚው የዶክተር ጌታቸው ተድላ መቅድም፣ የጸሐፊውን ታሪክ በአጭሩ የሚያስረዳ መግቢያን አካቷል። ይህም መግቢያ ጸሐፊውን የሚያውቋቸው የተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች በነበራቸው የዲፕሎማሲ ሚና ዙሪያ የሰጧቸውን ምስክርነቶች የሚያጠቃልል ነው። እነኚህ ነገሮች በአማርኛውም የመጽሐፉ አካል ተካተው ቢገኙ ለአማርኛ አንባብያን የበለጠ ጠቃሚ እንደሚኾኑ ግልጽ ይመስላል።

Read more
AyyaanaIrreechaa2009aa

A Day in Bishoftu:Errechaa a Quest for Identity?

Sunday morning is when the official ceremony starts. The multitude begins to move towards the lake and the tree, following a group of gray-haired ladies who clasp a handful of fresh cut grass in one hand and a long, thin ceremonial cane in the other. They sing together with a smooth and sweet sound–“Oh mareo mareo”–in a repeating chorus, (meaning, “we have come back again after a year”). They kneel down by the side of the water and touch the water with the grass in their hands, then sprinkle it on their bodies and on the people behind them. The people follow in their steps and the sprinkling continues. Fulfilling their vows by offering their gifts and prayers, people leave the side of the lake to make room for the newcomers.

Read more
Aba Poulos Statue

ያልተዳሰሱ የሐውልቱ ወጎች

ቀራጺው አቶ ብዙነህ ተስፋ ሐውልቱን እንዲሠራ ሲነገረው የተሰማው ደስታ ልክ አልነበረውም። ሐውልቱ የሚሠራላቸው ግለሰብ በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ስምም ይኹን ሐውልቱ ሊያመጣው የሚችለው ውዝግብ ለእርሱ አልተከሰተለትም። “ሰውየውን በጣም ነው የማደንቃቸው” የሚለው አቶ ብዙነህ የእኚህ ሰው የተማረ ሰብእናና በእርሱ አገላለጽ “ማቹርድ አስተሳሰብ” ይማርከዋል። የሐውልቱንም ዕድሜ በተመለከተ ሲነገር የነበረውን አምስት መቶ ዓመት አቶ ብዙነህ አያውቀውም። “እኔ እንዲህ ዐይነት ዋስትና አልሰጥም” ሲል ጫን ባለ አነጋገር የሐውልቱ ዕድሜ ያን ያህል ሊኾን አንደማይችል አስቀምጧል። ከዚህ በተጨማሪ ሐውልቱ የተሠራው ከናስ ነው የሚለውንም አስተያየት ያስተባብላል፤ ሐውልቱ የተሠራው ፋይበር ግላስ ከተባለ ግብአት ነው በማለት። ከዚህ ዐይነቱ ቁስ የሚሠራው ሐውልት ደግሞ ዕድሜው ከስድሳ እና ከሰባ አይበልጥም የሚለውን ግምቱንም ያስቀምጣል።

Read more

“የኤርትራ መዘዝ” ወይስ ዜና መዋዕል?

የመጽሐፉን አብዛኛውን ክፍል የያዙት “ነገረ ደርግ” እና “የሰሜን አካባቢ ችግሮች” የሚሉት ሁለት ክፍሎች ናቸው። በእነዚህም የመጽሐፉ አስኳል የኾኑ ክፍሎች ያለፈው መንግሥት ሥልጣን የያዘበትን ሁኔታ በጥቂቱ ከዳሰሱ በኋላ የኤርትራን ጦርነት የሚገልጹትን ታሪኮች አሳይተዋል። የጦርነት ታሪኮቹን ሲተርኩም የግብረ ኀይል፣ የቀይ ኮከብ ሁለገብ አብዮታዊ ዘመቻን፣ “ድብቁ” ዘመቻ፣ የቀይባሕርን እና የባሕረ ነጋሽን ዘመቻዎች ከዕቅዳቸው ጀምሮ ውጤታቸውን እና የውጤታቸውን ግምገማዎች ግልጽ በኾነ ቋንቋ አቅርበዋል።

Read more