የጠፋው ትውልድ [አንድ ለቅዳሜ]

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር ከትውልድ ጋራ አያይዘው ለመረዳትና ለመፍታት የሚሞክሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሉ። እርግጥ አንድ ትውልድ የአገርን ችግሮች በተለያዩ ምክንያቶችና የታሪክ አጋጣሚዎች ሊፈታ ወይም ሊያባብስ ይችላል። ሆኖም የኢትዮጵያን ችግሮችም ይሁን መፍትሔዎች በአንድ ትውልድ ሥራዎች ውስጥ መፈለግ/መጠበቅ ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ሊያደርስ ይችላል። በተጨማሪም ሐሳብን ለማደራጀት በትውልድ ቀመር እንነጋገራለን እንጂ ማንኛውም ማኅበረሰብ ሕይወትን የሚመራው በተለያዩ ትውልዶች ተሳትፎ ነው። በአንድ ትውልድ አባላት ብቻ የሚመራና የሚኖር የሕይወት አካል የለም።

የአገራችንን ፖለቲካ በትውልድ ለመረዳት ሲሞከር የውይይቱ ማዕከል የሚሆነው ክፍሉ ታደሰ “ያ ትውልድ” ያለው የአብዮቱ አንቀሳቃሽ ትውልድ ነው። የ “ያ ትውልድ” ብዙዎቹ አባላት አሁን ዕድሜያቸው በአማካይ ከ50-75 ነው። “ያ ትውልድ” ከ1960ዎቹ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ፖለቲካውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። በእርግጥ ለአንድ ትውልድ 40 ዓመት ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊ ሆኖ መቆየት እጅግ ብዙ ሊባል የሚችል አይደለም። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትውልድ አከፋፈል ላይ የተሠራ ጥናት አለነበብኩም፤ ባገኝ እጅግ እወድ ነበር። ለዚህ ጽሑፍ ያህል “ያ ትውልድ”ን መነሻ አደርጌ ሦስት ዘመኖችን አስቀምጫለሁ። ይህን ሳደርግ ግን ወደ ፖለቲካ ትውልድ አከፋፈል ዝርዝር ሐልዮቶች (ቲዎሪዎች) መግባቱ አስፈላጊ አልመሰለኝም። የትውልዱን መለያ “ስም”፣ የትውልዱን አማካይ የትውልድ ዘመን (ልደት)፣ ፍላጎቱ ገኖ የወጣበትን የፖለቲካ ዘመኑን (ፖለቲካ)፣ እንዲሁም የትውልዱ አባላት አሁን የደረሱበትን ዕድሜ (ዕድሜ)በቅደም ተከተል አስቀምጫጨዋለሁ።

 1. “ያ ትውልድ”፤ ልደት 1925-1950፤ ፖለቲካ 1960-1997፤ ዕድሜ 53-78
 2. “የጠፋው ትውልድ”፤ ልደት 1951-80፤ ፖለቲካ 1995- ፤ ዕድሜ 23-52
 3. “አዲሱ ትውልድ”፤ ልደት 1981-1990፤  ፖለቲካ፣ አልደረሰም፤ ዕድሜ 20-

ዛሬ ላነሳ የፈለኩት (ነገር ፍለጋ በሚመስል መልኩ) “የጠፋው ትውልድ” ስላልኩት የራሴ ትውልድ ነው። ይህ ትውልድ በመሠረቱ ስለ አገርም ይሁን ስለ ፖለቲካ ያለው አመለካከት በቅድሚያ የተቃኘው “እናት አገር” ወይም “ኢትዮጵያ” በሚለው ጽንሰ ሐሳብ ዙሪያ ነው። የ“እናት አገር”  ገናና ታሪክ፣ ሉአላዊነት እና አንድነት የፖለቲካው እንብርት ነበር። ስለ እናት አገር ለተከታዩ “አዲሱ ትውልድ” የሚተርፍ አክብሮትና ፍቅር ያደረበትም ለዚህ ነው። የአክብሮቱና የፍቅሩ መገለጫ ሁሉ “ትክክል” መሆኑን ግን እጠራጠራለሁ። አብዛኛው በተለይም ከተማ ቀመሱ በ”እናት አገር” ርዕዮተ ዓለማዊና ባህላዊ መሠረት ቢቀረጽም፣ በሒደት “በብሔረሰብ መብት” አስተምህሮ መማረክ የጀመሩ ቁጥራቸው የማይናቅ የትውልዱ አባላት አሉ።

የዘመኑ ፖለቲካ ለ“ለጠፋው ትውልድ” ስለ ነጻነት፣ ስለ ሰብአዊ መብት ወዘተ ይህ ነው የሚባል ሐልዮታዊም ሆነ ተግባራዊ ቁም ነገር የሚያስጨብጠው አልነበረም። በተቀራዊው የፖለቲካን አስከፊ ገጽታ “እያደነቀ” ለማደግና ለመኖር የተገደደ ነበር። በማንኛውም መመዘኛ ነጻነቱን እና መብቱን የተነጠቀ፣ ተስፋውን በቅርብ የማይመለከት፣ የአገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ በተግባር የኖረ ነው። በመሠረታዊ ተፈጥሯቸው ጨቋኝ የሆኑት ብዙዎቹ የፖለቲካ ቡድኖች (ደርግ፣ ህወሓት፣ ኦነግ፣ ሻእቢያ…) ለደም ግብር የጠሩትም እርሱኑ ነው። “ወይ በባሌ ወይ በቦሌ” ያለውም ይኸው የእኔ ትውልድ ነው።

በዘመነ ደርግ ትውልዱ ስለ ነጻነትና ስለዴሞክራሲ ከመስማትና ግፋ ቢል ከማሰብ ያለፈ ዕድል አልነበረውም። እርሱም ቀርቶበት ሁሉንም የሕይወቱን ገጽታዎች ለመቆጣጠር የሚደረገው ትግል ስርአቱ በማንም እንዲተካለት ከመመኘት አድርሶታል። ህወሓት/ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ጠንካራና የተደራጀ ሕዝባዊ ተቃውሞ ያልገጠመውም በዋናነት በዚህ ምክንያት ነው። ምናልባት ይህ የሆነው የትውልዱ አባላት በአብዛኛው ህወሓት/ኢሕአዴግን “እንደ ነጻ አውጪ ተቀብሎት” የሚመስለው ካለ ተሳስቷል። ሲጀመር ህወሓት/ኢሕአዴግ “የእናት አገር” አስተምህሮ ለመናድ እንደሚሰራ ሲናገር የቆየ ነው፤ በተጨማሪም አብዛኛው ሕዝብ ስለ “ነጻ አውጪዎቹ” ያለው መረጃ የወቅቱ መንግሥት የሚሰጠው ብቻ ነበር። ይህን ሐሳብ ያነሳሁት “የጠፋው ትውልድ” ለወሰደው አንድ መሠረታዊ ምርጫ መነሻ ምክንያት ስለሆነ ነው። ይህም ብዙ የትውልድ አቻዎቼ ለኢሕአዴግ እና በአጠቃላይም ለብሔር ፖለቲካ አራማጆች ዕድል መስጠት፣ ማዳመጥ እና ለመረዳት መሞከር እንደሚገባ ማመኑ ይመስለኛል። ከብዙ መሰሎቼ ጋራ የአገራችንን ታሪክ በብሔር መብት ጥያቄዎች አንጻር እንደገና የመገምገም፣ አዳዲስ እይታዎችን የማስተናገድ፣ የብሔር ጥያቄን በተለያየ ጥልቀትና አቅጣጫም ቢሆን የማሰላሰል (appreciate) ፖለቲካው ፈቃደኝነትም ድፍረትም አላጣንም። ቢያንስ በግሌ የብሔር ጥያቄን ከሚያነሱ ጋር እንደ ጥያቄው የምጋራቸው ብዙ ነገሮች አግኝቻለሁ፤ በአጀንዳው አቀራረጽና አቀራረብ፣ እንዲሁም በመፍትሔው ላይ ግን ልዩነቶች አሉኝ። ይህ ተሞክሮ ትውልዴን ይወክላል ብዬ መናገር ግን አልችልም። ዛሬ በብሔረሰብ በተደራቹ የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥ ስለ ኢትዮጵያ/እናት አገር ቀና አመለካከት ያለቸው ሰዎች በአብዛኛው የዚህ ትውልድ አባላት ሆነው ቢገኙ አይገርምም። በተቃራኒውም የብሔረሰብ መብት ጥያቄ በታሪካዊዋ ኢትዮጵያ ማእቀፍ ውስጥ ሊስተናገድ የሚችል ነው የሚሉም እንዲሁ።

ነካ ነካ ፖለቲካ

የጠፋው ትውልድ በዘመነ ደርግ ፖለቲካ የሚጠቀስ ተሳትፎ አልነበረውም። “ተሰብሰብ” ሲባል ይሰበሰባል፤ “ንቃ” ሲባል ይነቃል፤ “ዝመት” ሲባል ይዘምታል አለዚያም ታፍሶ ይዘምታል፤ “ጫካ ግባ” ሲባል ይገባል አለዚያም ተገዶ ይወርዳል…። ኢሕአዴግ ሥልጣን ሲይዝ የዚህ ትውልድ ፖለቲካዊ ፍላጎት እና እምቅ አቅም ምን ሊሆን እንደሚችል የገመተ አይመስለኝም። “የብሔር ፖለቲካ”  ጨዋታው ለሁሉም የፖለቲካ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሆን ሳያምኑም አልቀሩም። እነርሱ “ዴሞክራሲ” ሲሉና እኛ (የእኔ ትውልድ) ዴሞክራሲ ስንል ፈጽሞ ስለተለያዩ ነገሮች እናስብ እንደነበር የገባን ግን እየቆየ ሆነ፤ ለሁለታችንም። ለዚህም ነው ኢሕአዴግ እና ሌሎቹም ብሔር ተኮር ድርጅቶች በብሔረሰብ ፖለቲካ ሙሉ በሙሉ የሚያምኑ የትውልዱን አባላት እንኳን ማርካት ያልቻሉት። ምክንያቱም እነርሱ “የብሔረሰብ መብት” ሲሉ የምራቸውን ለዴሞክራሲ ይጠቅማል ብለው ነው፤ ኢሕአዴግና መሰሎቹ ደግሞ ገና እዚያ ገጽ ላይ አልደረሱም። በኢሕአዴግ የብሔር ፖለቲካ በመሳተፍ የመጀመሪያ ቅሬታ የደረሰባቸውም እነዚሁ የትውልዴ አባለት ነበሩ።

በሌላ በኩል የተቃውሞ ፖለቲካውን ጎራ የተቀላቀሉም የመረረ እውነታ ገጣሟቸዋል። እነዚህ ወገኖች በአንድ በኩል የኢሕአዴግ ዴሞክራሲ እነርሱ ከሚሉት የተለየ መሆኑን ቢያውቁም የአፈናው አይነትና መጠን ግን ከሚያስቡት ፈጽሞ የተለየ ሆኖባቸዋል። አንዳንዶቹም “ደርግ ሌላ ምን አደረገ?” ሲሉ መደመም ጀምረዋል። በሌላ በኩል በየፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ድርጅታዊ ሕይወትም ቢሆን ሌላ የትግል ሜዳ ሆኖ ጠብቃቸዋል። ፖለቲካን እንዲሸሽ፣ ከቀረበም በጥንቸል ንቃት እንዲንቀሳቀስ በሚያሳምን ድባብ ውስጥ ያደገው ይህ ትውልድ የዘመነ ኢሕአዴግን ፖለቲካ ለመሸሽ ብዙ ጊዜም ማስጃም አያስፈልገውም ነበር። እንደለመደውም የፖለቲካ ጫማውን አውልቆ  በቅርብ ተመልካችነት ተሰለፈ። ትኩረቱንም ወደ ሌሎች ዘርፎች አደረገ፤ ትምህርት፣ ንግድ፣ ቤተሰብ፣ ሃይማኖት፣ ስደት…። በዚህ ወቅት በፖለቲካዊ አቋሙ በማመናቸው ብቻ ኢሕአዴግን የተቀላቀሉ የዚህ ትውልድ አባላት እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።

“የጠፋው ትውልድ” በወሳኝ የሕይወቱ ጊዜ ከፖለቲካው መጽሐፍ ከመጥፋት የተረፈው በመርጫ 97 ዋዜማ ሆነ። ቀደም ሲል እንዳልኩት የአንድ ትውልድ አባላት ሚና የጎላ እንጂ ብቸኛ ሊሆን የሚችልበት ማኅበረሰባዊ ንቅናቄ ሊኖር አይችልም። በዚሁ እይታ ምርጫ 97ን ከሞላ ጎደል የዚህ ትውልድ አዲስ “አብዮት” አድርጎ መውሰድ ስሕተት አይመስለኝም። ይህ ማለት ከ“ያ ትውልድ”ም ይሁን ከ“አዲሱ ትውልድ” ለዚህ አዲስ የፖለቲካ ጅማሮ ወሳኝ ሚና የተጫወቱ አልነበሩም ማለት አይደለም። የምርጫ 97ን ወሳኝ መልእክቶች እና ሥራዎች በመሠረቱ የቀረጹት የዚህ “የጠፋው ትውልድ” ፖለቲካዊ ፍላጎቶች እና ምኞቶች ናቸው። የ“አዲሱ ትውልድ” የመጀመሪያ አባላትም ቢሆኑ የዚሁ መንፈስ ተቋዳሾች ሆነዋል። ይህን መልእክት በሚገባ ማንጸባረቅ የቻሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መሪዎቻቸው ጎልተው ወጥተዋል።

ምናልባት ይህ ታሪክ ሲነሳ ብዙ ጊዜ ቀድሞ የሚታወሰው “ቅንጅት” ነው። ሆኖም በብሔረሰብ ቢደራጁም “ጥያቄው በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ በመቀራረብ መፈታት ይችላል” የሚሉት ከፍተኛ ድጋፍ ማግኘታቸው መረሳት የለበትም። ይህ ደግሞ በመሠረቱ ብዙዎች “ቅንጅት”ን ለመደገፍ ያበቃቸው ምክንያት ሌላ ገጽታ እንጂ ፍጹም ተቃራኒ አይደለም። ቅንጅት ውስጥም ይሁን ከደጋፊዎቹ መካከል “የብሔረሰብን ጥያቄ” የማይቀበሉ ወይም እውቅና የማይሰጡ ሰዎች ይኖራሉ፤ አብዛኛው የዚህ ትውልድ አባል ግን የኢትዮጵያን አንድነትና የብሔር ጥያቄን ፈጽሞ የማይታረቁ ጉዳዮች አድርጎ አይመለከትም። በዚህ መነሻነት የሚቀርቡት መፍትሄዎች ሊለያዩ ይችላሉ፤ ቁም ነገሩ ግን ብዙው ሰው አጀንዳዎቹን የተረዳበት መንገድ ነው። በመፍትሔ አማራጮች ላይ መለያየቱ የዴሞክራሲን  አስፈላጊነትና ተቀባይነት ማግኘት የሚያሳይ ይሆናል። “ቅንጅት”ን የብሔረሰቦችን ጥያቄ እውቅና የማይሰጥ አድርገው የሚያቀርቡት ኢህአዴግን የመሰሉ ጠባብ ድርጅቶች እና አንዳንድ የራሱ የቅንጅት ጭፍን አባላት ብቻ ይመስሉኛል። ከዚያ ውጭ በሕዝቡ ውስጥ የነበረው “የቅንጅት መንፈስ” የዴሞክራሲ፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የመቻቻል እና የመተማመን እንጂ የመጠራጠር፣ የጥላቻና የመናናቅ አልነበረም። እንዲዚያ ባይሆን ኖሮ የራሱ የህወሓት/ኦህዴድ/ብአዴን… አባላት ሳይቀሩ ለ“ቅንጅት” ድምጻቸውን ባለሰጡ ነበር።

ይህንን እውነታ “የጠፋው ትውልድ” ከደረሰበት ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበረሰባዊ ደረጃ አንጻርም ማየት ወደ ተመሳሳይ መደምደሚያ ሊያደርሰን ይችላል። የትውልዱ አባላት በትምህርትና በእውቀት፣ በሥራ/ገቢ እና በማኅበራዊ ኑሮ ወሳኝ የሚባል ተሰሚነት ለመፍጠር ጊዜ አግኝተዋል። ይህ ተጽእኖ በወላጆቻቸውም ሆነ በልጆቻቸው/ታናናሾቻቸው ላይ መንጸባረቁ የማይቀር ነው። የትውልዱ ፖለቲካው ምልከታ በቀኝም ይሁን በግራ የተሰለፉትን የፖለቲካ ጎራዎች መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማስተናገድ የሚሞክር በመሆኑ በቀላሉ ለማጣጣል የሚመች አልነበረም። አሁን አሁን ሳየው ግን በቅንጅት ውስጥ ሳይቀር ይህ መንፈስ ዘልቆ ያልገባቸው “ትልልቅ”ም “ትንንሽ”ም ሰዎች ነበሩ። የ“ቅንጅት መንፈስ” ግን የዚህ ትውልድ አንድ ሁነኛ የፖለቲካ ፍላጎት ነጸብራቅ ሆኖ ሊቆይ እንደሚችል እገምታለሁ፤ ግምት ነው።

ያስተሰርያል

ምናልባት “የጠፋውን ትውልድ” ፖለቲካዊ ምኞት የሚወክል አንድ ነገር ጥቀስ ብባል መጀመሪያ ከሚመጡልኝ ነገሮች አንዱ የቴዲ አፍሮ “ያስተሰርያል” ነው። የዚህ ዘፈን ልቀት ግጥሙ ወይም ዜማው አይመስለኝም፤ መልእክቱ ነው። አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ! በነገራችን ላይ ቴዲም የዚሁ “የጠፋው ትውልድ” አባል ነው። የምርጫ 97 መንፈስ ቀደም ሲል እንዳልኩት በመሆኑ ይፈልግ የነበረው “ስርየትን” ነበር፤ ደም የማይፈስበት ስርየት። አለመታደል ሆኖ መሣሪያውን የታጠቀው የፖለቲካ ቡድን ስርየትን ያለደም ማሰብ የማይችል ድንጉጥ አማኝ ነው፤ ስለዚህም ደም ፈሰሰ፣ ለዚያውም “ስርየት” ላያመጣ።

የነጻነትን እና የዴሞክራሲን “ስርየት” ያለ ደም መፍሰስ ማግኘት እንዳልቻለ የተመለከተው “የጠፋው ትውልድ” በምርጫው ማግስት ብዙ ዋጋ ከፈለ። ይህን ተከትሎም እንደገና ወደ ጥንቸል ስጋቱ ተመለሰ። ኢሕአዴግም አገዘው፤ በአንድ በኩል ከጥቅማ ጥቅም ጋራ የተያያዘ የምልመላ ስትራቴጂ አምጥቷል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በተቃዋሚነት ቀርቶ ብዙዎችን ሊያደራጅ በሚችል መልኩ የተለየ አስተያየት መያዝ የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍ እንዲል አድርጓል። በቤተሰብ፣ በንግድ፣ በትምህርት ወዘተ ሐላፊነቶች የተያዘው “የጠፋ ትውልድ” ፖለቲካን በጥንቸላዊ ጥንቃቄ ወደማየቱ መመለሱ ወደ ቀደመ ቤቱ እንደመመለስ ነው። ነገር ግን የአሁኑ ዘመን የተለየ ነው፤ አፈናውን ማቅለልና ማለፍ የሚችልባቸው አማራጮች አሉ። ስለዚህም እንደ ደርግ ዘመን መንግሥት የሚለውን ብቻ የመስማት ግዴታ የለበትም፤ ፖለቲካዊ ተሳትፎውንም በተለያየ መልኩ “ስሙን ሳይገልጽ፣ ድሙጹን ሳያሰማ” በለሆሳስ መቀጠል ችሏል።

የኢሕአዴግ አያያዝ “ያለደም ስርየት የለም” የሚለውን የብሉይ ሕግ የሚያጸና ሆኗል። ለታይታና ለዲፕሎማሲያዊ ፍጆታ ከሚሆነው በቀር እውነተኛ የዴሞክራሲ እና የመቻቻል ምልክቶች ጨርሰው ሊጠፉ የቀራቸው እጅግ ጥቂት ነው። “ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን ያለ ደም ማምጣት ይቻላል ወይስ አይቻልም?” የሚለውን ክርክር በድጋሚ የፖለቲካችን ቁልፍ አጀንዳ እያደረገው ያለውም ራሱ ኢሕአዴግ ነው። “የጠፋው ትውልድ” ተስፋውን አልጣለም፤ ከደርግ ጊዜ በተለየ ፖለቲካዊ ሐሳቡን በሰላምና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ማረመድ ስለመቻል አለመቻሉ ግን እርግጠኛ አይደለም። ስለዚህም በክርክሩ መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆሟል። በፖለቲካው ተስፋ ቆርጦ ሌላ ሕይወቱን ስለማሸነፍ ብቻ ለማሰብ የወሰነ አለ፤ ፖለቲካውን እንደ ትግል በማየት ተሳትፎውን የቀጠለ ጥቂት አለ፤ የሚከፍለውን ዋጋ በሚቀንስ መንገድ በዴሞክራሲ ግንባታ መሳተፍ የሚመኝ ነገር ግን መንገዱ ጠፍቶት ግራ የተጋባ አለ፤ ራሱን ኢሕአዴግን በመቀላቀል ጥቅማ ጥቅሞችን እያገኙ በዚያውም ከውስጥ ለውጥን መጀመር ይቻል እንደሆነ ብሎ የሚያስብም አይጠፋም…። የኢሕአዴግን አመራር እያደነቀ “ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር” የሚል የዚሁ ትውልድ አባል የማያውቅ ሰው ካለ አንዱን ድረ ገጽ ይጎብኝ።

“የጠፋው ትውልድ” የሽግግር ዘመኖች ትውልድ ነው፤ ለዚያውም የከሸፉ ሽግግሮች። ይህ ጠቃሚ ጎኖች ቢኖሩትም ጉዳቶችም አሉት። አንዱ ጉዳቱ ትውልዱ በፖለቲካው ውስጥ አሻራውን የሚተውበት እድልና ጊዜ ማጣቱ ነው። ሆኖም ይህ ትውልድ ደርግ እና ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ መኖር ያልነበረባቸው፣ ድጋሚም መምጣት የሌለባቸው የፖለቲካ ስርአቶችና አመራሮች መሆናቸውን ኖሮ አይቷቸዋል። ይህ ትውልድ ሁሉንም ፖለቲካዊ ጽንፎች በአያቶላዎቹ ሲተነተኑ ሰምቷል፤ በፊት አውራሪዎቹ ሲተገበሩ አይቷል፣ ኖሯቸዋልም። ይህ ትውልድ የፖለቲካ ሐላፊነቱን ካልተወጣ አገራችን አዳዲስ ደርጎች እና አዳዲስ ኢህአዴጎችን ማስተናገዷ እንደማይቀር እሰጋለሁ። ያን ጊዜ ብዙ መንግሥቱዎች ወይም ብዙ መለሶች ይወሩናል፤ አያርግብንና! “የጠፋው ትውልድ” ከዚህ ልምድ የሚቀስመው ትምህርት አገሪቱን ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚያሸጋገር ቀመር እና ፖለቲከኞች እንዲያፈራ ይረዳው ይሆን? እስከዚያ ድረስ “እንደ ጠፋ” ትውልድ እንቆጥረዋለን፤ ልክ በጣም አልፎ አልፎ እንደምናገኘው ሰው፤ “ምነው ጠፋህ?” እንደማለት! አይዞን!

Twitter Digg Delicious Stumbleupon Technorati Facebook Email

18 Responses to “የጠፋው ትውልድ [አንድ ለቅዳሜ]”

 1. hi mesfin
  as usual it is a good observation.
  I also feel that these generation is the generation to make a sacrifice for political change.
  But we are unfortunate that we havent reached to a stable political system but onthe other hand,if we really appreciate a challenge,this is the generation on the right time to fled the dictators on our sholder with all sacrifice.
  regarding change,it is very very clear that it is not possible with peaceful transition

 2. In almost all the statements you wrote what you want it to be, rather than what it is!
  Since you are one sided politician you can NOT write fair analysis about Ethiopia, you are ignorant about thoughts on the other side of the river yet.

  At beginning you said,’u do not have enough evidences on some issues but you have confidential allegations’. Be careful the way you conclude about people’s thoughts, it does not mean you know all about a society since all your friends are alike.

  • Dear Nelson,
   Thanks for the comment. Only for the purpose of constructive engagement, let’s say all you have said about me and the article is true. What is your point, anyways? What do you have to share with us so that I can understand “thoughts on the other side of the river”? If you cannot give us some perspective and information, your comment has no value in it. Save the labeling for another forum.

 3. ብራቮ መስፍን: በጣም ጥሩ ትንተና ነው!!!

  ያለፈው ትውልድ በኢትዮጵያዊነትና በብሔረሰብ ፖለቲካ ተከፋፍሎ ብዙ ደም መፋሰስ ከደረሰ በኋላ በብሔር ፖለቲካ ደጋፊዎች የበላይነት ጦርነቱ ተጠናቀቀ:: በእርግጥ አስከፊ እልቂትና ደም መፋሰስ በኢትዮጵያዊነት በሚያምኑ የፖለቲካ ቦድኖች መካከልም ተካሂዷል (ምናልባትም ለኢትዮጵያ አንድነት ፖለቲካ አራማጆች መሸነፍ አንዱ ምክንያት ይሄ ሊሆን ይችላል):: የሚያሳዝነው ደርግ ከወደቀ በኋላ እንደታየው በአርግጥ ያሸነፈው ፖለቲካ የብሔር ፖለቲካ ወይም ፌዴራላዊነት ብቻ ሳይሆን: ትግሬነትም ጭምር ነው:: በግልፅ እንደታየው ዋናው የፖለቲካው ቅራኔ መሰረት የብሔረሰብ መብት ሳይሆን: በትግሪኛ ተናጋሪና በአማርኛ ተናጋሪ የንጉሳውያንና የባላባት ቤተስቦች መካከል የነበረው የስልጣን ፉክክር ተቀጥያ በዘመናዊ የፖለቲካ ቃላት ተሽሞንሙኖ ነው:: ህወሐትን የመሰረቱትና የሚመሩት ሰዎች ማንነትና አመለካከት ይሄንኑ በግልፅ ያሳያል:: በመሆኑም ሌሎች የብሔረሰብ ፖለቲካ አራማጆች (በዋነኛነት ኦነግ) ተመልሰው ወደ ጫካቸውና ወደ ሰደታቸው እንዲገቡ ሆኗል::

  ‘የጠፋው ትውልድ’, የነ ቴዲ አፍሮ ትውልድ ከዚህ ብዙ የተማረ ይመስለኛል:: በአንፃሩ አሁንም በ ‘ያ ትውልድ’ ተፅዕኖ ስር የወደቀና ለኢትዮጵያውያን ሰላምም ሆነ ዲሞካራሲ ማምጣት ባልቻለው ያለፈው የፖለቲካ ተሞክሮ ውስጥ የሚዳክር አሁንም አለ:: ቢሆንም ‘ያ ትውልድ’ አልፎ ብሩህ ተስፋ: ራዕይና ቆራጥነት ያላቸው የ ‘የጠፋው ትውልድ’ አባላት (እንደ ብርቱካን ያሉት) ችቦውን አንስተው ፋናውን የሚወጉበት ጊዜ ግን ሩቅ እንዳልሆነ በአርግጠኝነት መናገር አችላለሁ:: ጊዜ ሁሉን ያሳየናል:: ይሄንን የተረዱ የአጥፊው ‘ያ ትውልድ’ አባላት የአጥፍቶ ጠፊ ሴራቸውን እየወጠኑ እንደሆነ እገምታለሁ:: ቢሆንም ያንንም አልፋ ኢትዮጵያ ትቀጥላለች::

  በነገራችን ላይ ቱኒዚያ ውስጥ የታየው የሄንኑ እውነት ያረጋግጣል::

 4. Well, I like the analysis. But to think about sacrifice to bring changes is unlikely. Reasons follow.
  1. There are still outdated groups like OLF who will always work against the
  interest of their own people and country.

  2.The mentioned “the lost generation” is coward,ignorant and undemocratic. Look at your self, you fled the country for fear of arrest when you could positively affect millions up to now. this is cowardice. Most of those who cries hagere, ethopia minamin is fake. They could even sell her in a day if they get money out of it.

  3.The New Generation is under the complete influence of the ruling party.
  4.EPLF will always work against us

  The only way to bring change in ethiopia is by convining people in the ruling party and by empowering the peaceful struggle. by assuring that EPRDF leaders that they will be safe even if they are out of power. If we want to revenge them, that means they were right to revenge the Derg/country when they took power.

  Any option out of this, even if happend(unlikely), may not result in what the people want.

 5. Dear Mesfin

  Thanks for the response.

  I hope you were not expecting comments only which endorse your idea. And also appreciation for your engagements, No way of undermining it. The document is well articulate and good solution is proposed, but your documents (Not only this one) always preach negative about the other bank of the river. I advise you not to completely neglect postive taskes done (e.g by the organizations/groups you mentioned as undemocrat) You can not bring a change to a nation like that. I do not know how democrat you will be with such sided attitude, if you were given the chance.
  BTW I will say the same thing for the groups on the other side of the river. My point is for the good of Ethiopia both should be on same boat and move down stream together, even scarifying some of the their radical thinkings. But in your papers I see NO readiness (that where the labeling came from) to be on the boat, even if such people same old thinking are on the boat they will cause problem since they stick to their original idea.

  God bless a nation for its people!

 6. I am one of those people who worked for Kinijit and you label chifin. Can you provided evidence that kinijit supported ethnic politics?
  A couple of observations:
  1. All opposition organization accept federalism but not ethnic federalism. It is important to clearly understand what ethnic federalism is and its detrimental impact to a stable democratic order. Issues of national oppression such as language, culture etc can best be addressed with a constitution begin with the “we the people”, not “the nations, nationalities and peoples”. You need to understand that those of you label as chifin do not object to equal treatment of language and culture. We just believe that objective can be achieved without creating division and resentment among the different groups. We also believe rights including language right should be vested in individuals irrespective of where they leave or what ethnic group they are from.
  2. Your claim that ethnic opposition organizations received significant support needs some scrutiny. It is important to realize that for the last 50 years the politics of ethnic politics has dominated the political space. In such a situation the only surprise is that an organization that advocated the primacy of individual rights and refused to work with ethnic organizations dominated the results. Election 2005 is a watershed event that cannot be discredited by diluting its essential ideology or the success of ethnic organizations.
  3. Change in Ethiopia will only come when we have an organization that discounts the slogans of the student movement and organize around issues central to the individual. Ethiopians of your age and younger would benefit from the early days of America. I will leave you with my favorite: “We hold these truths to be self-evident, that all men are created equal, that they are endowed by their Creator with certain unalienable Rights, that among these are Life, Liberty and the pursuit of Happiness.”

  • Dear Jibo,
   Thank you for the comment.I must admit that the word “chifin” was unnecessary in my article as my purpose is to invite discussion, not offending. You purposely misquote me, however, to advance your argument as if I called all members “chifin.” However, minus the derogatory sense of the term, I stood by my assessment regarding those people.I can assure you there were members of Kinijit who was not even willing to hear the name of an ethnic group and political questions related with it. Though my participation has never been of a party member, I had quite good opportunities to meet many members.In that I had a better chance of understanding the existence of strands of political attitudes among the ranks and files of Kinjit from outside.
   I have no problem with the idea of putting Individual Rights at the center of the analysis. If you recognize the existence of “national oppression” in one way or the other, we are on the same page.
   Another important point regarding “Kinijit” is no one, including those of you participated in the party, cannot claim monopoly of ownership of the “kinijit spirit” and it’s meaning. Kinijit was many things at a time for different people. The beauty of Kinijit was this reality of embracing strands of opinions under one umbrella- Democratic Ethiopia.
   2. I think you’re convinced that Kinijit won the 2005 election by some 99.6%. Not at all. Indeed Kinjit garnered a significant portion of the vote. It’ll be erroneous if we assume that credible “Ethnic based” organizations such as OFDM (Bulcha) and OPC (Merrera)had no support. Indeed these organizations are,more or less, advocate their policy within the Ethiopian framework, which will again give a credit for the pro-kinijit movement.
   It is deep in my heart that liberty, life, and the pursuit of happiness are essential rights of all individuals. Yet, we cannot answer questions of ‘group rights’ by simply undermining the issue and voices. We must come up with a sympathetic heart and creative mind to mend the wounds. That is the message my generation want to hear!

 7. mesfin i like your ideas.I’m sure Nelson is not from the lost generation because he doesn’t know the pain of this generation.we wounded a lot we don’t know how and when going to heal

 8. በአንድ በኩል “የጠፋው ትውልድ ” ንቃ ሲባል የሚነቃ፣ ዝመት ሲባል የሚዘምት ሲታፈስ የሚታፈስና እራሱን እንኩአን ለመከላከል የማይችል ወዘተርፈ አይነት ትውልድ ሆኖ ይቀርባል። በሌላ በኩል ደግሞ ” እናት ሀገር” “ሉዓላዊነት “ኢትዮጵአዊነትም” የዚሁ ትውልድ ” የጋራ ዕሴቶች” እንደነበሩ ይነግረናል ። አንድ ጊዜ ጫማውን እየሰቀለ ሌላ ጊዜ ደግሞ እያጠለቀ ሲያሻው” ስለዲሞክራሲና ስለነፃነት” የሚነግረኝ አልነበረም የሚለው ትውልድ የራሱን ተጠያቂነት ፣ራስወዳድነቱንና ፣መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁነት ማጣቱን ግን ወደ ቀዳሚው ትውልድ ጣቱን በመቀሰር” ለመሸወድ ” ይሞክራል ። ምናልባትም ትውልዱ” ነፃነትን ፣ፍትህንና ዲሞክራሲን ” ከአንድ ጀምበር ኮንሰርት የሚጠብቅ ብቻ ሳይሆን ስለአነዚህ እሰቶችም ያለው እውቀት ከኮንሰርት የተቀዳ እሰክሚመስል ድረስ ። ” ነፃነት ፍትህና ዲሞክራሲ ‘ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን ለማስረዳት “ያ ትውልድም ” ሆነ ቀዳሚዎቹ የከፈሉትን ዋጋ (በጥሩም ይሁን በመጥፎ ጎኑ) አቅልሎ መረዳት ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ትውልድም መፍትሄ አይመስለኝም ። “ምነው ጠፋህ ?” ብሎ ጠያቂው ማንይሆን?”አይዞን”
  ባዩስ?ማህበራዊ ፣ኤኮኖሚያዊ ፣ፖሊቲካዊና ስነልቡናዊ ቀውስ ውስጥ ያለፈና የሚያልፍ ትውልድ አለ ግን “የጠፋ ትውልድ “የለም ።

 9. እንደምን አላችሁ አዲስ ነገሮች
  ምን ያህል አድለኞች ነበርን ሁሌም ቅዳሜ ቅዳሜ ብናገኛችሁ እንድዚህ አይነት ከፍ ያለ ትንትና ማን ሞከረ:: (ለ ኢትዮቻናል ዳረጋቹን)
  መስፍን በዚሁ ቀጥል::

 10. It is all about me. I need change. I am desparate with this government (የኢሕአዴግ አያያዝ “ያለደም ስርየት የለም” የሚለውን የብሉይ ሕግ የሚያጸና ሆኗል) and i have no hope on the others.
  ይህ ትውልድ የፖለቲካ ሐላፊነቱን ካልተወጣ አገራችን አዳዲስ ደርጎች እና አዳዲስ ኢህአዴጎችን ማስተናገዷ እንደማይቀር እሰጋለሁ.
  How could we full fill our responsibilty?
  This is my question everyday specially this days.

 11. It is not hard to acknowledge some accomplishments by the government. I think they have serious commitment to development. If only, they would think we, the people, were not bothering them with silly ideas like free media, free elections, separation of party and government structure/ resources…

  There is always more than one side on every argument. But, that does not mean both or all are right. Our country’s government is not democratic.

 12. bella, got me wrong!
  About your healing I do not really see any one ready to implement democracy in Ethiopia. All are waiting some gap to practice their rigid idea (non-ethinic federalism or whatever). So you may NOT heal soon. I think you have sensed it too.

 13. Understanding the new youth: Interesting…

  If you have observed some of the clips in the “Tunisian Popular Uprising” these days, the youth is its undisputed pillar, like it was no doubt four decades ago in Ethiopia – unfortunately without any prior precedence and indigenous national political experience, with the disasterous outcome as we know, for all the protagonists and the people in the final effect. When one day Ethiopia comes to the pleasure of hosting such a change towards an enlightened social order, it is of paramount signifiance understanding the new youth appropriately; and the sooner the better – The new youth, which has today fortunately a lot of prior experiences at its disposal (*1 albeit failures at several levels, from which it can learn and nurture its political course, if only it is ready to invest its moral and intellectual courage in the due reflections, at the latest beginning from today (2*.

  The following article of “Addis Neger”
  Addis Neger 15.01.2011:
  የጠፋው ትውልድ [አንድ ለቅዳሜ]
  is interesting in this perspective.
  *
  http://berhane-aymero.blogspot.com/2011/01/understandning-new-youth.html

 14. A good and intellect observation. Of all Addis Neger team, I am a fan of you followed by Girma, Tamrat and Masresha. You know how to make different notions intuitive.
  The keenness to bring political, economical and social change of both YETEFAW and ADDISU generation has overwhelmingly dehydrated. Crave for new style of leadership: accountable, transparent, benign, benevolent governance has been crashed. After the disputed 2005 election, everything has changed. The government’s attitude towards its fellow citizens is murky, gloomy. The only thing it intends is to make every generation YETEFAW TEWLDE. In such kind of situation, I am pessimist about ADDISU generation’s capacity. በብዛት ስለ ሀገሩ ጠንቅቆ የማያውቅ፣ ከወይራ እሳት የተወለደ የወረቀት አመድ ነው አዲሱ ትውልድ፡፡ ይኽ ንግግር እኔንም ሊጨምር ይችላል-ማለቴ ችግሩ የጋራ ስለሆነ የሚያሳስብ እና የሚያሳዝን ነገር የለም፡፡ Neither does YETEFAW generation can be competent enough to create sober Ethiopia. The query should be directed to: what kind of maverick intellects and politicians do we need? Should we be adamant and condemn about the squandered times of our lives? Shouldn’t our politicians study Ethiopian history and foundation so they can endorse major and fundamental principles of Ethiopia? Instead of dwelling on the shortcomings of others, and paying due attention to the dark side of our history, it is better to firmly stand up united. But still the riddle remains unfolded. How should we work united when the politics has managed to evade, obstruct and abolish trust amongst each other? Well, time will give the answer. ለሁሉም ጊዜ አለው፤ለመዋደድም ጊዜ አለው፤ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ለማፍረስም ጊዜ አለው፤ለመጣመርም ጊዜ አለው፤ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ለመጻፍ ጊዜ አለው፤ለማንበብም ጊዜ አለው፤አዲሱ ትውልድ ለመሆን ጊዜ አለው፤የጠፋው ትውልደም ለመባል ጊዜ አለው፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

 15. Mesfin,
  If I misquoted you it was not intentional. A couple of observations:
  1. The point is not whether Kinijit won 99% or 51% and there was not claim of that in my response. The most important point is ethnic politics that dominated the political discourse of Ethiopia lost in spite of its unbridled access to media and resources. TPLF/EPRDF and the ethnic opposition could only produce marginal victory (even if we allow the vote stealing) over the politics of individual liberty.
  2. You seem to be convinced that the solution for Ethiopian politics lies in solving the question of national oppression. I can agree that national oppression is potent and significant force for the political elite but not for average Ethiopian. But I suggest the path to the solution for national oppression goes only through individual liberty. You seem to think within the framework Yatiwild. I believe the problem with Ethiopian politics is that we continue to think within the discredited politics of student movement.
  3. Last I suggest our relationship to each other or to the government should not be derived by our past/history whether national oppression or something else. Our future should based on the society we want to create. To be clear we should address injuries of the past. The important idea is this solution is a contributor to our vision. An example is the issue of language. Those of us opposing to ethnic politics do support individuals to have the right to speak their language at school, at the court or anywhere or even for Ethiopia to have multiple national languages. The point of departure on the strategy for the implementation of this worthwhile effort. I believe this should be done in a way that will keep Ethiopia united and democratic. That leads me to call for these rights to be vested in the individual while mandating the government to provide the vehicles for the exercise of this right. Liberty applies only to the individual not to a nation, nationality, etc. Only when the individual is free will the issue of national oppression withers. I believe the politics of Kilil practiced by Meles or Bulcha or Merera or Hailu Shawel will neither grant liberty to the individual nor end national oppression.

 16. Hi Mesfin, a great piece of work and thumbs up for your reflection. Here comes my comments:

  As I’ve tried to read some academic works on issues of generations and interactions between and among generations, there are some people who argue that there is a tendency to have a relatively ‘silent’ or ‘passive’ generation immediately after an ‘influential’ generation. And they give some practical examples by taking the case of most African countries (or other countries for that matter) where the independence period generation stayed longer in maintaining the political and economic power without serious challenge from the immediate followers in spite of the gross misdeeds and problems. On the other hand, one of the core elements considered in identifying a generation is the ‘shared generational consciousness’ and this consciousness is built within the socio-historical, political, cultural and economic structures and realities constructed by the former generation. And as it is witnessed in our country’s case, the kind of structural hurdles that EPRDF is creating, mainly economic (through patronage), are intended to ensure its existence beyond the present time. And what I feel is that, it is not only from EPRDF that the generational influence is coming but from the other political groups as well and it’s up to us to live up to the ‘reality’ and contribute our part constructively. For me, the “Addis Neger Generation” (I dare to say), is one of the manifestations of the actual capability of ‘the lost generation’,.. there are lots of things happening around (in the minds of people, across the social network sites, within political parties, in our art (music and literature)…and so on….) and I would say let’s keep it up…..

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.