በኦሮሚያ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አርሦ አደሮች መሬት እየተነጠቁ ነው

(ሙሉ ገ.)

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የገጠር ዞኖች ውስጥ የኦህዴድ – ኢሕአዴግ ፓርቲን “በአባልነት አንቀላቀልም “ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋፊ አርሶ አደሮች መሬታቸውን እየተነጠቁ፤ የመብት ጥያቄ ያነሱትም ለእስራት እየተዳረጉ መኾኑን የአዲስ ነገር ምንጮች ገለጹ። ይኸው የመሬት ነጠቃ እና የማፈናቀል ተግባር በተለይ በኢሉባቦር፣ በምዕራብ እና ምሥራቅ ወለጋ፣ በቦረና እና የጉጂ ዞን የገጠር ቀበሌዎች እና ዞኖች ተጠናክሮ መቀጠሉን እነዚሁ ምንጮች አስረድተዋል።

በኦሮሚያ ክልል በሻኪሶ ወረዳ ያሉ የአዲስ ነገር ምንጮች እንዳስረዱት ከኾነ በአካባቢው የሚገኘው በሼሕ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን ባለቤትነት የሚንቀሳቀሰው “ለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ድርጅት” በዙሪያው ከሚገኙ አርሶ አደሮችን መሬት ወስዶ ካሳ ሊከፍላቸው አልቻለም።

የመብት ጥያቄ በማንሳት ወደ ዞኑ አስተዳደር አቤቱታቸውን ለማሰማት የሄዱ ከሁለት መቶ በላይ የሚኾኑ የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ተፈናቃዮች “ኦነግ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እና ልማት አደናቃፊ” በሚል ተወንጅለው ለእስራት መዳረጋቸውንም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።

ከሻኪሶ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው “ለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ድርጅት” በዙሪያው ያሉትን የገበሬ መሬቶች ለማስፋፊያነት ጠቅልሎ የያዘ ሲኾን፣ ሌሎች የኦህዴድ -ኢሕአዴግ አባላት ተደራጅተው የመሠረቷቸው ኢንተርፕራይዞች ደግሞ ከለገደንቢ ማስፋፊያ ጎን ለጎን ያሉ መሬቶችን ለባሕላዊ የማዕድን ሥራ እንዲያውሉት ተሰጥቷቸዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢህአዴግ ፓርቲ ሰዎች እየተመሠረቱ ያሉ ኢንተርፕራይዞች በአዶላ ሬዴ ወረዳ ጭምር እየገቡ በሰዎች ማሳ ላይ “ምርምር” እንደሚያደርጉም ታውቋል። “የማሳው ባለቤት የኾኑ ገበሬዎች ሲጠይቋቸውም ደብዳቤ ከወረዳ እና ከዞን ይዘን ስለመጣን ልትከለክሉን አትችሉም” በሚል እንደሚያስፈራሯቸው ይናገራሉ።

በምርጫ 2002 ዋዜማ አካባቢ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በነበሩት አባዱላ ገመዳ አደራዳሪነት ተካሂዶ የነበረው የሻኪሶ ዙሪያ ወረዳዎች ነዋሪዎች እና የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ድርጅት ባለቤት ሼሕ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን የደረሱበት ስምምነት ምንም ውጤት እንዳላመጣ ሐሳባቸውን ለአዲስ ነገር ያካፈሉ የሻኪሶ አካባቢ የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ።

በወቅቱ አላሙዲን በአካል በስፍራው በመገኘት ከአካባቢው ሰዎች ጋራ የተወያዩ ሲኾን፣ ከአካባቢያቸው መሬት ተጠቃሚ ያልኾኑትን በሻኪሶ ዙሪያ የሚገኙ 15 ወረዳዎች ለእያንዳንዳቸው በነፍስ ወከፍ አንድ ሚሊዮን ብር ለልማት ሥራ ከመመደብ ባሻገር ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች እና ለኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ነዋሪዎች ደግሞ አንድ ከፍተኛ የቴክኒክና ሞያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ለመገንባት ቃል ቢገቡም እስካሁን “በተግባር የታየ ነገር የለም” ብለዋል።

ከዚህ ጋራ በተያያዘ በ“ቦረና – ጉጂ ደን ድርጅት” የልማት እንቅስቃሴ ሰበብ መሬታቸውን ከተነጠቁ  አርሶ አደሮች መካከል ዕድሜያቸው ከ70 እስከ 85 ዓመት የሚኾናቸው አረጋውያን  የሚገኙበት ሲኾን፣ ግብር የከፈሉበትን ሕጋዊ ማስረጃ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የኦሕዴድ- ኢሕአዴግ ካድሬዎች ከተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አርሶ አደሮች መሬት ለመንጠቅ የሚጠቀሙበት “ መሬቱን ለደን ልማት፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለማዕድን ማውጣት” በሚል ሰበብ ቢኾንም “ መሬቱ ደን ሳይለማበት፣ ማዕድንም ሳያወጣበት በግላጭ የኦህዴድ አባል የኾኑ አርሶ አደሮች ሲከፋፈሉት እንደሚታይም የዞኑ ምንጮች ገልጸዋል።

በሕገ-ወጥ መንገድ መሬታቸውን የተነጠቁ ገበሬዎች መብታቸውን ለመጠየቅ ወደ ዞን አስተዳደር በሄዱበት አጋጣሚ “ሕዝብን በመንግሥት ላይ ታነሳሳላችሁ” ተብለው መታሰራቸውም ታውቋል። “በገንዘብም ከ ሁለት ሺሕ እስከ 15 ሺሕ ብር የተቀጡ ገበሬዎችን ተመልክቻለሁ” ብለዋል ምንጮቻችን፡፡

የኦፌዴን ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋሳ ለአዲስ ነገር እንደተናገሩት በኢሊባቡር ዞን ዳሪሙ ወረዳ ውስጥ ነዋሪ የኾኑት አቶ እስማኤል ሁሴን “ያለ ፈቃዴ የኦህዴድ አባል አልኾንም በማለቱ ብቻ በዓመት 20 ኬሻ ቡና የሚያመርትበትን የእርሻ መሬቱን ተነጥቆ ለኢሕአዴግ ካድሬ ተሰጥቶበታል” በማለት ለፓርቲው ከደረሱት ከ200 በላይ ሪፖርቶች መካከል አንዱን ዋቢ አድርገው ጠቅሰዋል።

Twitter Digg Delicious Stumbleupon Technorati Facebook Email

5 Responses to “በኦሮሚያ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አርሦ አደሮች መሬት እየተነጠቁ ነው”

 1. I wish if I know what journalists at home would say about this. I hope it is done to their knowledge. By the way my concern does not include the journalists of the government owned media and its proxies in the name of the independent papers.

 2. Shek Alamoudin is a guise, we know who realy loots Ethiopian wealth behind this so called investor. The Sheik has a store of experience when he helped the Royal families of Saudi embezzle and transfer the nations wealth from the public domain to their own coffer. Another law-abiding business men like Haile G/Sillasie are also being wooed to give a cover-up to Woyane’s blood money in the name of partnership. Many of the seemingly high growing business companies such as ‘Sunshine real estate’ have also lent a hand in this plunder.

 3. It is a shame that EPRDF is uprooting the farmers based on their political opinion. It is one thing to rob of people their basis means of survival – land and it is another thing to make it a punishment for what they think and hold in their minds and hearts. This is genocide and Meles is a professional who has perfected the crimes against humanity and genocide of the Oromos and the Ogadenis just like his predecessor. This is being perpetrated when the “haves” are being given EFFORT’s profit money to build the buildings in cities. It is sad to be an Ethiopian under Meles.

 4. Makelawi Torture 23 December 2010 at 4:09 am

  The Constitution of Ethiopia Article 25 states that a person’s political opinion or position or his gender or ethnicity would not be a standard when it comes to the government’s doinig its business. Now what we are seeing in the country is the favouritism of Tigrians and EPRDF members to get whatever comes through the government – donor aid, non-appointment professional jobs, land allocation, tax exemptions, Kebele housing, and what not. the government is dancing on the Constitution and burning the Constitution like the terrorists burn flags. The EPRDF is the one that should be held accountable and this investigation is long overdue. Meles should not be allowed to trample upon the Constitution and roar like a lion only when to whip his enemies by exploiting the Constitution as if he respects it for one second. Investigate Meles and do justice to the helpless.

 5. Where are all the people who believe in the ‘peaceful struggle’, they are onducting? Ghandi’s or MLK’s way?
  Oh! I know where they are. They are sitting and waiting, may be I should say preparing for he next election.
  May God help them.
  I know the people will eventually reject them unless they are there for them in the time of their need.

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.