የመንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ከግል ጋዜጦች ጋር በ“ሰጥቶ መቀበል” መርህ ሊሰራ ነው

(ሙሉ ገ.)

በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው የመንግስት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ መንግሥት በወሰደው አሉታዊ እርምጃዎች እየተዳከመ እና እየተመናመነ የመጣውን የግል የህትመት ሚዲያ በማስታወቂያ በመደገፍ ልማታዊ ዘገቦችን እንዲያስተላልፉ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀመረ።

የጽህፈት ቤቱ የአዲስ ነገር ምንጮች “ሰጥቶ መቀበል” ሲሉ የገለጹት ይህ አሰራር የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለግሉ ሚዲያ ማስታወቂያ እንዲሰጡ  ማበረታታት እና በምላሹ በመንግሥት የሚሰጠውን የዜና ጥቆማ እና የልማት ሂደቶችን በስፋት እንዲዘግቡ የሚያደርግ ነው፡፡

“የህትመት ሚዲያው መመናመንና መዳከም መንግሥትን እያስተቸው ነው” ያሉን አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልደፈሩ የጽህፈት ቤቱ ሰራተኛ “አሁንም ቢሆን ግን መንግሥት ከሚዲያው የሚፈልገው  ሰጥቶ መቀበልን ነው” ይላሉ፡፡

ይህንን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ ጽህፈት ቤቱ አንድ የሥራ አመራር ኮሚቴ ማዋቀሩን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ የግል ሚዲያ የሥራ አመራር ኮሚቴው የተቋቋመው በጽህፈት ቤቱ የሚዲያ ግንኙነትና የውጭ ጋዜጠኞች ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ስር ነው። ጽህፈት ቤቱ የግል የህትመት ውጤቶች ከማስታወቂያ ጋር በተያያዘ ያለባቸውን ችግር ለማወቅ የሚያስችል መጠይቅ ለሚዲያ ተቋማት በትኗል፡፡

በጽህፈት ቤቱ የኤሌክትሮኒክስና የህትመት ሚዲያ ልማት  ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀው መጠይቅ ወደ ጥያቄዎች ዝርዝር ከመግባቱ በፊት ዓላማውን ያስረዳል። መጠየቁ የተዘጋጀው “የግል የህትመት ሚዲያዎች  የፌደራል መንግስት ማስታወቂያዎችን በማግኘት ረገድ ያሉባቸውን ችግር በመለየት በቀጣይ የማስታወቂያ ስርጭት ፍትሃዊነትን በጠበቀ መልኩ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦችን በማካተት የአሰራር ስርዓት  ለመዘርጋት ነው”ሲል ሰነድ ይተነትናል።

መጠይቁ ስድስት ጥያቄዎችን ይዟል። “የፌደራል መንግስት መስርያ ቤት ማስታወቂያዎችን ምን ያህል ያገኛሉ?” የሚለው የመጀመሪያ ጥያቄ አራት አማራጮችን አስቀምጧል።  “አነስተኛ”፣ “መካከለኛ”፣ “ከፍተኛ” ከሚሉት አማራጮች በስተመጨረሻ “እያገኘን አይደለንም” የሚል ተቀምጧል።  ሚዲያዎቹ ምንም የማይገኙ ከሆነ ምክንያቱ ምንድነው ብለው እንደሚያምኑ ተጠይቀዋል። የፌደራል መንግስት ማስታወቂያዎች ተጠቃሚ ከሆኑ ደግሞ በምን መንገድ ማስታወቂያዎቹን እንደሚያገኙ ያስረዱ ዘንድ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

የመንግስት ማስታወቂያዎች ለግል ሚዲያዎች የሚደርሱበት አሰራር ፍትሃዊ መሆን አለመሆኑም በመጠይቁ ተካቷል።በጥያቄዎቹ ማጠቃለያ የተቀመጠው ደግሞ “የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ማስታወቂያዎች በምን ሁኔታ ቢከፋፈሉ ጥሩ ነው ብለው ያስባሉ?” የሚል ነው።

የመንግስት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ከመንግሥት ጋር በትብብር ለመሥራት ፈቃደኝነታቸውን ያሳዩ ጋዜጦችን ህዝቡ በገበያ ቢቀጣቸው እንኳ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከሚሰጧቸው የማስታወቂያ ገቢ በተጨማሪ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋዜጣቸውን በቋሚነት በመግዛት የገበያ ስጋታቸው እንደሚቀረፍ ማስጠናቱን  ምንጮች ለአዲስ ነገር ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም (የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን)፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የመሳሰሉ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለህትመት ሚዲያ ማጠናከሪያ እንዲውል በቋሚነት ማስታወቂያ ለጋዜጦቹ እንዲሰጡ አቅድ ተይዟል።

Twitter Digg Delicious Stumbleupon Technorati Facebook Email

6 Responses to “የመንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ከግል ጋዜጦች ጋር በ“ሰጥቶ መቀበል” መርህ ሊሰራ ነው”

 1. If the Berket office proceeds on the plan and gives ad opportunities it would be good for the private press and readers at large. After all the money comes from the public finances which orignally should be used to the public good rather than glorifying TPLF.

  Let the press benefits finanically from the scheme. We the readers know how to deal with the so called Limatawi Zegebawoch. At the end of the day the seteto mekebel scheme will be ‘seteto mekemet’ thanks to the ignorance of bereket and co who thought money will buy everything.

 2. Is this another version of TPLF’s attempt to co-opt the private media?

 3. Is it ‘Reporterization’ of other independent medias?

 4. Another DECEIT. I have an idea,, they should start with ‘Awramba Times’ as they have with ‘Reporter’. Woyanes are the smartest people on earth,, but the rest of the world is dumb (that is Woyanology)!!

 5. This is very funny.

  This is the “Lematawi Communication Strategy” that emanates from the great mind of Meles and Berekt??????

 6. Lucy in America 1 January 2011 at 5:49 pm

  This is the part and parcel of TPLF’s 5 years transformation plann. In the coming five years all mini free presses must join TPLF’s camp by this or aonther way.Bereket [mberatu] g/hiwot would you go back to school and finish atleast high school. How could you be a minister from 9 grade?

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.