የአገር ቤት ጋዜጦች ምን ጻፉ?

ፍትህ ጋዜጣ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ

ፍትህ፡- ብርቱካን ከፓርቲያችሁ ለቀቀች እንዴ? እረፍቷ አልበዛም? ወይስ ማለቂያ የሌለው እረፍት ነው?

አቶ አንዱዓለም፡- ብርቱካን ያሳለፈችው መከራ ብዙ ነው፡፡ የበርማ ጄነራሎች እንኳ ሳንሱኪን ያሰሩበት ኹኔታ ከብርቱካን ጋር አይነጻጸርም፡፡ የብርቱካን የከፋ ነው፡፡ የእኛ መሪ ተብዬዎች የበርማ ጄኔራሎችን ያህል እንኳ ሆደ ሰፊነት የላቸውም፡፡ ለስድስት ወራት ያህል ሰው በማይታይበት፣ መፀዳጃ ባልነበረበት አደገኛ ቦታ አስረው ሥነልቡናዋን ለመስበር ሞክረዋል፡፡ እስር ቤቱን አውቀዋለሁ፡፡ ታስሬበት ነበር፡፡ የእርሷ ግን እኔ ከማውቀው እጅግ የከፋ፣ ከበርማ ጄኔራሎች ሁሉ እጅግ የከፋ፣ እኩይ ሥነ-ምግባር በተጠናወታቸው ሰዎች የተወሰደባት ርምጃ ነው፡፡ ሰማይ እንኳ እንዳታይ መስኮት ያልነበረው ክፍል ውስጥ ነው መጀመርያ ላይ ያሰሯት፡፡ እናም በቂ እረፍት ያስፈልጋታል፡፡

ፍትህ፡- /ያለፉ ነገሥታትን ከአቶ መለስ ጋር ያነጻጽሩልኝ፡፡/

አቶ አንዱዓለም፡- ‹‹…አቶ መለስን ብትወስዳቸው ባንዲራን ሲያንቋሽሹ፣ የሦስት ሺሕ ዓመት ታሪክን ሲያንቋሽሹ፣ በታሪክ ማንም መሪ አገሩን ቅኝ ገዥ ብሎ የማያውቀውን እርሳቸው አገሬ ቅኝ ገዥ ነበረች ለማለት የደፈሩ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ማንም አድርጎት የማያውቀውን ገንጥሉልኝ ብለው የለመኑ ናቸው፡፡ በበኩሌ የአቶ መለስ የልጅነት ጊዜ ሥነ-ልቡናቸው ሊጠና ይገባል እላለሁ፡፡ ከኢትዮጵያ አንድነት ጋራ ለምንድነው እልህ የሚገቡት ለሚለው ጥያቄ መልስ ሊገኝ ይችላል፡፡››

ሚሊንየም አዳራሽን ለመከራየት ስንት ብር ያስፈልጋል?

ቁም ነገር መጽሔት በዚህ ወር ዕትሙ ሚሊንየም አዳራሽ ለአንድ ቀን ለመከራየት ስንት ብር እንደሚያስፈልግ ጽፏል፡፡ አዲስ ፓርክ እና ማኔጅመንት ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የሚያስተዳድረው ሚሊንየም አዳራሽ የሚሊንየም በዐሉ ‹‹አልጫ›› እንዳይኾን እገዛ አድርጓል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን /ምናልባትም እስከሚቀጥለው ሚሊንየም/ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ያስተናግድ ይኾናል፡፡ በሚሊንየም አዳራሽ አልሳምን የመሰሉ ባለሀብቶች ልጃቸውን ድረውበታል፡፡ ብዙ ቴሌቶኖች ተሰናድተውበታል፡፡ እነ ሪሃናን፣ ኤከንን እና ቢዮንሴን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ዘፋኞችም ተውረግርገውበታል፡፡  አቶ መለስም ከክብርት ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ ጋራ ወዝወዝ ያሉት በዚሁ አዳራሽ ነው፡፡ ይህ አዳራሽ ለአንድ ቀን ለመከራየት ካሰቡ 354ሺሕ ብር ይፈለግብዎታል፤ ለያውም ከቫት በፊት፡፡

ግብረሰዶም የፈጸመው ኢትዮጵያዊ በዘጠኝ ዓመት እስራት ተቀጣ

የ32 ዓመት ጎልማሳ የኾነው ቴዎድሮስ አራጌ ግብረሰዶም የፈፀመው ላምበረት አካባቢ ሲኾን ተጠቂው የ15 ዓመት ወጣት በምግብ እና መጠጥ ግብዣ ተታሎ ሰክሮ እንደነበረ ተዘግቧል፡፡ ወንጀለኛው ታዳጊውን ካሰከረው በኋላ ፊቱን በጨርቅ በመሸፈን ጥቃቱን ፈጽሞበታል ሲል ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

አዲስ ሲኒማ ቤት በመስቀል አደባባይ

ታኖራሚክ ሲኒማ ይባላል፡፡ በሼሕ አላሙዲን ብር በተገነባው  የቀይ ሽብር ሰማዕታት ሐውልት ሥር ይገኛል፡፡ መያዝ የሚችለው 200 ሰዎችን ብቻ ነው፡፡ ኾኖም ሳምንቱን ሙሉ የአገር ውስጥ ፊልሞችን ያቀርባል፡፡ ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ ጠዋት ጠዋት ለሕፃናት የሚኾኑ ፊልሞችን ያቀርባል፡፡ ሲኒማ ቤቱ ከትንሽነቱ ባሻገር ዘመናዊ እንደኸኮነ የአገር ቤት ጋዜጦች ዘግበውለታል፡፡

ይርዳው ጤናው ከሮዝ መጽሔት ጋራ

ጥያቄ፡-አሜሪካ ትቀራለህ የሚባል ወሬ ነበር፡፡ እንዴት መጣህ?

ይርዳው፡- አዎ! እንዲያውም ወደዚህ ስደውል ‹‹አንተ ለማታየው አገር እጅ ትሰጣለህ እንዴ?›› ብለውኛል፡፡

ጥያቄ፡- ይኹኔ በላይ ቤት የገጠመህ ነገር አለ ይባላል፡፡ እስኪ እሱን አጫውተኝ

ይርዳው፡- ግብዣ አድርጎልኝ ቤቱ ተገኘሁ፡፡ ስለቤቱ አንዳንድ መግለጫዎችን ይነግረኛል፡-‹‹…ምን መሰለህ በጣም  ጥሩ ቤት ነው፤ በዚህ በኩል ባር አለ…›› እያለ፡፡ ወደታች ስንወርድ ደግሞ እንዲህ አለኝ፡- ‹‹ ቤቱ እኮ ይገርመሃል… እንዴት ላሳይህ››

ሌላው ቬጋስ ውስጥ ክለብ እየሠራሁ አንድ ወጣት መጣና ‹‹…ይርዳው በዐይን አታውቀኝም፤ ተሾመ አሰግድ ጓደኛዬ ነበረ…›› አለኝ።

የዓመቱ አስገራሚ ቃለመጠይቅ?

ሮዝ መጽሔት ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ የሚባል ጋዜጠኛ አለው፡፡ ቶዎድሮስን የመጽሔቱ ስቲቨን ሳከር ልንለው እንችላለን፡፡ ስም የገነቡ እንግዶችን እያቀረበ በጥያቄ ያጣድፋቸዋል፡፡ በዚህ ወር እንግዳ አድርጎ ያቀረባቸው ሰው አቶ የማነ ወ/ማርያም ይባላሉ፡፡ የኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት መሥራች ናቸው፡፡ ከቴዲ አፍሮ ጋራ ድህነትን ለማጥፋት የሚለውን ኮንሰርት በአዘጋጅነት ሰርተዋል፡፡ ቃለ መጠይቁ እጅግ ሕልም የሚመስሉትን የአቶ የማነን አስገራሚ ምላሾች ይዟል፡፡ ለምሳሌ ፡-

 • ‹‹ወደ ስድስት ወር ከለማኞቹ ጋር አብሬ እየዋልኩ፣ እያደርኩ፣ እያጨስኩ፣ እየቃምኩ ማጥናት ጀመርኩ››

‹‹…ቀድሞውንም ሀብት የነበራቸው ወደልመና የገቡ፣ ታክሲ፣ ገልባጭ መኪና፣ የእርሻ ቦታ ያላቸው፣ ቤት የሚያከራዩ…እነዚህ ሰዎች ሀብቱን በልመና ያገኙ ሳይኾን ቀድሞውኑ /ሀብቱ/ ኖሯቸው ወደልመና የገቡ ናቸው፡፡ ሁለት ሚኒባስ ያላቸው ለማኝ ጓደኛ አሉኝ፡፡ መንገድ ላይ ተገናኝተን ታክሲ ልንሳፈር ስንል ቆይ ቆይ አትግባ ይኼ የኔ ታክሲ ነው ብለውኛል፡፡››

 • ‹‹ብትወድም ባትወድም 90 በመቶ የሚኾኑት ለማኞች ችግራቸው የግንዛቤ እጥረት እና የልብ ተነሳሽነት ማጣት ነው፡፡”
 • ‹‹አዊ ዞን ብትሄድ መሬቱ ለም ከመኾኑ የተነሳ ጭቃውን ልትበላው ትችላለህ፤ ሰዎቹን ጉንጫቸውን ስትነካው ስርጉድ ስርጉድ የሚል ነው፡፡ ግን ኡራኤል ጋራ ሲለምኑ ታገኛቸዋለህ፡፡››
 • ‹‹ትግራይ ብትሄድ አዲግራት የሚላስ የሚቀመስ ነገር የለም፡፡ መሬቱ ራሱ ምንም አያበቅልም፡፡ ግን በአዲግራት አካባቢ አንድም ለማኝ አታገኝም፡፡››
 • ‹‹..ላረጋግጥልህ… በርግጥ ላረጋግጥልህ፤ ጠበቅ ብዬ ስናገር በርግጠኝነት ሳይኾን ከርግጠኝነትም በላይ ነው፤ ለማኞቹን ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁ …ልመና ከሦስት ዓመት በኋላ ከዚች አገር ይጠፋል፡፡››
 • ‹‹… ይችን ቃሌን ይዘህ ከሦስት ዓመት በኋላ የምንገናኘው ልመና በሌለባት ኢትዮጵያ ነው፡፡ ምናለ በለኝ የዛሬ ሦስት ዓመት ስሜታዊ ኾናችኋል ባልከው አነጋገር ታፍራለህ፣ በጣም ይቅርታ ብለህም ትጠይቀኛለህ፡፡››
 • ‹‹…ከዛሬ ሦስት ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሳንቲም ሳንቲም እያለ የሚለምን ሰው አታገኝም፡፡››
 • ‹‹በኤልሻዳይ እምነት ለለማኝ ገንዘብ የሚሰጡትን ነፍሰ ገዳይ አድርገን ነው የምናያቸው፡፡ እሱ እንዲጸድቅ እና ሞተው ዐጽማቸው የቀረ ዘመዶቹን ወደ ገነት ለማስገባት ሰውየው የሱን ትራፊ እና ቅራሪ እየበላ ሥራ እንዲተው እያደረገው ነው፡፡››
 • ‹‹ቤት ሠርተው የአረጋውያን የምንትስ የሚሉትን በጣም እንቃወማቸዋለን፡፡ በተለይ አረጋውያን እነርሱ ቡናቸውን እየጠጡ ከማኅበረሱቡ ጋራ እንዲኖሩ ነው የምንፈልገው፡፡ ተመሳሳይ ሰዎችን በግንብ አጥረህ ማስቀመጥ ከሰብአዊነት ውጭ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ከትልልቅ ባለ ሀብቶች እና ባለሥልጣናት ለመዋጋት መሣርያችንን ወልውለን ነው የተቀመጥነው፡፡››
 • ‹‹ሕፃናቶቻችን የኢትዮጵያ ልጆች ለፈረንጅ /በጉዲፈቻ ስም/ ከሚሰጡብን ሁላችንም ብንሞት ነው የሚሻለው፡፡››
 • ‹‹ይኼን ሰውዬ/መለስ ዜናዊን/ በግል አውቀዋለሁ፤ እርሱ ራሱ ሺሕ ቢኾን የታሰበውን ሁሉ/ትራንስፎርሜሽኑን/ መፈጸም ይቻል ነበር፡፡ ግን ከታች ያሉት አስፈጻሚ አካላት ናቸው ችግር የሚፈጥሩበት፡፡ …/እንደ መለስ ሺሕ ቢኖር …አሄሄ…መቶ ቢኖርም አገሪቷ ትለወጣለች…ኸረ ዐሥሩም/የአቶ መለስ ዐይነት ቢኖር/ ተአምር ይሠራሉ፡፡››
 • ‹‹ እኔ ሰውየውን /አቶ መለስን/ አምነዋለሁ፤ በቃ፡፡ እንደ በሽታም እንደማምለክም ልትወስደው ትችላለህ፡፡››
 • ‹‹መለስን…›› ሰዎች ያልተረዱት ሰው ይመስለኛል፤ ቢረዱት ኖሮ ሁሉም ሆ ብለው ይደግፉት ነበር፡፡››
 • ‹‹አንዲት ሴትዮ በትልቅ ስብሰባ ላይ የማነ ይኼን ዓላማ ይዘህ ትግሬ ባትኾን ደስ ይለኝ ነበር አለችኝ…መለስን የምወደው በትግሬነቱ፣ በትግሬነቴ አይደለም …››

‹‹…ጋሽ አዲሱ ለገሠ ከሥልጣን ላይ ሲወርድ ሳለ ጉባዔውን እጅ ነስቶ ሲቆም ሳየው በጣም በጣም እዝን ድብን ነው ያልኩት፡፡ ምግብ አልበላሁም፡፡ እንቅልፍ ሳላገኝ ነው ያደርኩት፡፡ ለምን እንደኾነ አልገባኝም፡፡ በጣም ነው ሰውየውን የምወደው፡፡ ንፁሕ ምንም የሌለው ለራሱ ምንም የማያስብ፣ ምንም ምንም የሌለው ነው፡፡ ከበረሃ እንደገባ እስካሁን ድረስ ያለው አዲሱ ለገሰ ነው፡፡

 • ‹‹…በነገራችን ላይ ከሦስት  መት በኋላ እኔ በሕይወት ላልኖር እችላለሁ፡፡ ምክንያቱም ያለኝ ዕድሜ የአምስት ስድስት ወይም ሰባት ዓመት ነው፡፡››

የአገር ቤት ምርቃት

 • ‹‹ከምርጫ 97 በኋላ ወደ ፌዴራል የዞረው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ወደ አስተዳደሩ ተመለሰ፡፡›› ሰንደቅ ጋዜጣ
 • ‹‹ብዙ ሺሕ ወታደሮችን ከሻዕቢያ ያስመለጡት ብርጋዴር ጄኔራል ዐርአያ ዘርዐይ አረፉ፡፡›› ፍትህ ጋዜጣ
 • ‹‹የዓለም የሳቅ ንጉስ በላቸው ግርማ ሰው ገጭቶ በማምለጡ የሰባት ወር እሥራት ተፈረደበት›› አዲስ አድማስ
 • ‹‹የመኢአድ ስድስት አባላት ጠፉ›› ሰንደቅ ጋዜጣ
 • ‹‹በአገር ፍቅር ቴአትር ትንሿ አዳራሽ የታየው ፊልም ከፍተኛ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናትን በእንባ አራጨ›› ሮያል መጽሔት
 • “የኢቲቪ ዋነኛው ተግባር ማብሰር ሲኾን የተመልካቾቹ ቋሚ ተግባር ደግሞ ማረር ነው፡፡” ሰንደቅ በትዝብት ዐምዱ
 • ‹‹ዞረች አሉ በማሳለጫ፤ በቤተመንግሥት እንዳትንጫጫ›› አውራምባ  ጋዜጣ ስለታላቁ ሩጫ ያሰፈረው ስላቅ
 • ‹‹መስከረም 11 ቀን 1998  ‹‹ልደቱን ያልያዘ ፓለቲካ ፖለቲካ አይደለም›› አልክ፤ መስከረም 14 ከሦስት ቀናት በኋላ ‹‹ልደቱ ከሃዲ ነው›› አልክ፡፡ በሦስት ቀን ውስጥ የአቋም ለውጥ ማድረግ አይከብድም? ፍትህ ጋዜጣ ለአቶ አንዱዓለም አራጌ /የአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ ያቀረበው ጥያቄ፡፡
 • ‹‹ሃያት አሕመድ አውሮፕላን አብራሪ ልትኾን ነ ነው፡፡››  ሮያል መጽሔት
Twitter Digg Delicious Stumbleupon Technorati Facebook Email

11 Responses to “የአገር ቤት ጋዜጦች ምን ጻፉ?”

 1. Ato Yemane spoke of the ‘Agaw Beggars’ in Addis, and compared the situation with the ‘absence of non-beggars in Adigrat’. What a confusion! who is being compared ‘Addis Vs Adigrat’ or ‘Agaws Vs Tigres in Adigrat’? Is he the leader of an NGO with a vision? Where did he put the other beggars in Addis (the Amaras and Tigres)? The man is lost in euphoria,, never to awaken,,
  I would like to repeat the nice excerpt◦‹‹አንዲት ሴትዮ በትልቅ ስብሰባ ላይ የማነ ይኼን ዓላማ ይዘህ ትግሬ ባትኾን ደስ ይለኝ ነበር አለችኝ…

 2. Very nice Update!

 3. Am confused.how and becouse of what Teddy Afro gave that fund for this man.

 4. ልመና ከሦስት ዓመት በኋላ ከዚች አገር ይጠፋል፡፡››
  ◦‹‹… ይችን ቃሌን ይዘህ ከሦስት ዓመት በኋላ የምንገናኘው ልመና በሌለባት ኢትዮጵያ ነው፡፡ ምናለ በለኝ የዛሬ ሦስት ዓመት ስሜታዊ ኾናችኋል ባልከው አነጋገር ታፍራለህ፣ በጣም ይቅርታ ብለህም ትጠይቀኛለህ፡፡››

  I like that. lol

  • ‹‹… ይችን ቃሌን ይዘህ ከሦስት ዓመት በኋላ የምንገናኘው ልመና በሌለባት ኢትዮጵያ ነው፡፡ ምናለ በለኝ የዛሬ ሦስት ዓመት ስሜታዊ ኾናችኋል ባልከው አነጋገር ታፍራለህ፣ በጣም ይቅርታ ብለህም ትጠይቀኛለህ፡፡››

   then…

   ‹‹…በነገራችን ላይ ከሦስት መት በኋላ እኔ በሕይወት ላልኖር እችላለሁ፡፡ ምክንያቱም ያለኝ ዕድሜ የአምስት ስድስት ወይም ሰባት ዓመት ነው፡፡››

   is he mentally retarded person?

 5. ◦‹‹መስከረም 11 ቀን 1998 ‹‹ልደቱን ያልያዘ ፓለቲካ ፖለቲካ አይደለም›› አልክ፤ መስከረም 14 ከሦስት ቀናት በኋላ ‹‹ልደቱ ከሃዲ ነው›› አልክ፡፡ በሦስት ቀን ውስጥ የአቋም ለውጥ ማድረግ አይከብድም?

  I would rather say you must be one smart guy to be able to see so quick how shrewd that man is.

 6. OMG!!! What is wrong with MR. Yemane? is he insane?

  I cannot believe he is the one who worked with tedy Afro

  Abolishing begging in three years from Ethiopia?

  ANO! YOU MUST BE KIDDING…

 7. የየማነ አረጋዊን ቃለምልልስ እኔም ሳነበው በጣም አስቆኛል:: ለእናቴ ስነግራት “በሦስት ዓመት ሦስት እጥፍ አያድግ ብለህ ነው::” ከሱ ፊደል ቆጣሪነት የሷ ልምድ ይሻላል:: በነገራችን ላይ ሰውየው በጣም ዘረኛ ነው:: ልመናን ስለማጥፋት ሲያወራም የሚያወራው የትግራይ ተወላጅ ለማኞችን እያሰበ ነው:: ልብ ብላችሁ መጽሄቱን አንብቡት::

 8. i really like it … thank you for updating us!!!!

 9. if Mr Yemane didn’t tell us he chewed kat and smoked weed/whatever, i would be surprised by his answer.
  by the way now i know who’s advising meles zenawi lol.

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.