አዲስ አበባ መስተዳደር በቢፒአር አስጠንቶ ተግባራዊ አድርጋለሁ ያለውን መርኀ ግብር አጠፈ

(ሙሉ ገ)

በአቶ ኩማ ደመቅሳ የሚመራው የአዲስ አበባ መስተዳድር በ2003 ዓ.ም የበጀት ዓመት የዲግሪ ምሩቃንን በመቅጠር በዐሥሩም ክፍለ ከተሞች ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ላይ በመመደብ እና በቦታው ላይ ብቃት ጎደላቸው ባላቸው ሠራተኞች ምትክ ብቁ የኾነ የአሠራር ለውጥ ለማምጣት በቢፒአር አስጠንቶ ተግባራዊ አድርጋለሁ ያለውን መርኀ ግብር አጠፈ።

አርብ ሕዳር 3 ቀን 2003 ዓ.ም ከመስተዳድሩ ለዐሥሩም ክፍለ ከተሞች የወረደው መመርያ እንደሚያሳስበው ክፍለ ከተሞች በበጀት ዓመቱ በቋሚ ቅጥር ሂደት ላይ የያዟቸውን ምሩቃን ሁሉ ውል እንዲያቋርጡ በማዘዝ፣ ቀድሞ በነበረው የሰው ሐይል ሥራው በአግባቡ እንዲቀጥል አሳስቧል። በአጠቃላይም ከ1500 በላይ የሚኾኑ ጊዜያዊ  ሠራተኞች ውላቸው ተቋርጦ  ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የስንብት ደብዳቤ እንዲደርሳቸው የኩማ አስተዳደር ውሳኔ አስተላልፏል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በአስተዳደር ሥራ ላይ የተሰማሩ የዜና ምንጫችን ለአዲስ ነገር ሪፖርተር እንደገለጹት በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለውን የደመወዝ ጭማሪ በማስላት በጀት ለመቀነስ ሲባል ብቻ የተወሰነው ውሳኔ ወጥነት የጎደለው እና በመስተዳድሩ ውስጥ ሥራን ለሞያተኛ ብቻ በመስጠት ቀልጣፋ የኾነ አገልግሎት ለማምጣት የሚያስችለውን በጎ ጅምር የሚያጨናግፍ ብለውታል።

ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ለሞያተኞች ከፍ ያለ ግምት መስጠት የጀመረ መስሎ ነበር የሚሉት እኚኹ የአዲስ ነገር ምንጭ መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (ቢፒአር) ተካሂዶ በተጠናው ጥናት መሠረት ለልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች የሚያስፈልጉንን የሞያተኛ ዐይነት እና ብዛት እንዲሁም የቢሮ ቁሳቁሶች ዝርዝር አሳውቀን ነበር ብለዋል።

በዚሁ መሠረት በተያዘው የበጀት ዓመት አዲስ የቢሮ አደረጃጀት ያካሄድን ሲኾን መስተዳድሩም ለሥራ የሚያስፈልጉትን ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ስካነሮች፣ የፎቶ ኮፒ ማሽኖች እና የቢሮ ጠረጴዛዎችን አሟልቶ ስለነበር ቅጥር አካሂደን አብዛኞቹ ሠራተኞች በሥራ ላይ እንዲሠማሩ ተደርጓል። ቀሪዎቹን ደግሞ በቅርቡ ሥራ እንዲጀምሩ የሚል ዕቅድ አውጥተን በመጠባበቅ ላይ ነበርን። ሥራ ሳይጀምሩ ስድስት ወር የኾናቸውን ተጠባባቂ ለሥራ የተዘጋጁ ሞያተኞች ከወዲሁ እንድናሰናብታቸው እና ውል እንድናቋርጥ ከመስተዳድሩ ትዕዛዝ ደርሶናል ሲሉ ገልጸዋል።Twitter Digg Delicious Stumbleupon Technorati Facebook Email

5 Responses to “አዲስ አበባ መስተዳደር በቢፒአር አስጠንቶ ተግባራዊ አድርጋለሁ ያለውን መርኀ ግብር አጠፈ”

 1. Now that the election is over who cares. They will be reinstated after five years.

 2. አየ ወያኔ ! አገር ሲሽጥ መዋሸት፡ ሰው ሲገድል መቅጠፍ፡ ምርጫ ሲያካሂድ ማታለል፡ ታሪክ ሲጽፍ መዋሸት፡ የስራ አቀጣጠሩም ዘረኝነተና ጎጠኝነት… ከፋራነት ወደ አራዳነት ! “Revolutionary” ለውጥ ይሉአችሁ ይህ ነው ! አሞት ያለው ይስማ ወኔ ያለው ያዳምጥ። መፍትሄው-ተደራጅቶ ሁለ ገብ ትግሉን ማፋፋም ንው። ቁጭ ብሎ ማልቀሱ ፋይዳም የለው ! ንቀውናል እኮ ! ፈሪዎች፡ ትምክተኞች ፡ ጉረኞች፡ ጨቁዋኞች….ምን ያለተባልንው አለ። ፕሮፌሰር አስራትን በ 75 አመታቸው በጥፌ መተዋቸዋል እኮ ! እነ ሽብሬን በጠራራ ፀሐይ ደፍተዋቸዋል እኮ… ከዚህ በላይ ሞት ምን አለ?

 3. it is remembered that these compatriots were hired, by woyane at the eve of election time,on off hand manner to achieve a deliberate goal of garnering casual support .It was with this concealed motive that their employment effected.We have ,however ,uncovered time and again the criminal act of woyane and how exploits the situation for his political end .Like wise what kuma had done was anticipated right from the begining and did not come as surprise to those who have sufficient knowlege and read every bits woyanes move .Now woyane seem to be in its commanding height and complacent of its “achievement” of “winning 99.6%” parliament seat by snatching at a gun point and Jerrymandering.I think the service of these 1500 guys was needed only temporarily until woyane consolidated its illegitimate power.However i still remain suspicious that these guys may be fired on account of being Ethiopians of non-Tigryga speakers .
  Because no where in the present day Ethiopia Tigryans (ofcourse there are few)become victims of their own government.So the question is how long woyane cheat us?do we should allow to continue and put his shit on our heads.Is it not high time to lock hands and fight woyane ?Let us do our best collectively and individually in digging the grave of woyane before vanishes our country inour very face.

 4. EPRDFs same old silly stories …………. i think Kuma is in a state of paranoia……….. belive me this govt is making a great mistake ever…. these people in the worda were the cadres. They devout there time to this lair government during the election time………… finally Weyane like Lucifer turn its face to these poor cadres which were helping them in the crucial time…………… leka ewnet nebere Abyot lejochwan tebelalech yetebalew…..

 5. Name (required) 19 November 2010 at 8:16 am

  አይ ወያኔ እኔ ግን ምንም አይገርመኝም ዶ/ር ብርሀኑነጋ
  በ አንድወቅት የተናገሩትን ማሰታዋሰ ብቻ በቂ ነዉ //
  // እነዚህ ስልጣናቸዉን ለአንድቀን ለማራዘም የመያደርጉት እና የማይናገሩት የለም//

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.