ዲቪ እና CV

(አሮን ፀሐዬ)

የገጠር የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነኝ፡፡ መታወቂያዬ ላይ ከስሜ ትይዩ “ሌክቸረር” የሚል ማዕረግ አለበት፡፡ ኑሮ እና ሕይወቴ ግን ማዕረግ አልባ ነው፡፡ ደሞዜ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ብር ይደርሳል፡፡ ይህ ብር ግርማ ሞገሱ አፍ ይሞላል፡፡ ሲኖሩበት ግን ወፍ ነው፤ ይበራል፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድሮ የገቡትን ቃል እሳቸው ባያሟሉትም እኔ በራሴ ልወጣላቸው ብዬ በቀን ሦስቴ ያማረኝን ልብላ ብዬ በተውተረተርሁ ቁጥር ወር ሳይደርስ በዱቤ እጥለቀለቃለሁ። አስተማሪ ካልበላና ካላነበበ ራሱንም ትውልድንም ይገድላል፡፡ በርግጥ ማንበብ ከተውኩ ዘመን የለኝም፡፡ መብላት ግን መተው የማኢቻል ኾኖብኝ ይኼው አለሁ።

በደሞዜ ላይ 160 ብር የቤት አበል ጠብ ይደረግበታል፡፡ አንዲት አነስተኛ ክፍል ተከራይቼ፣ አነስተኛ ምግብ በልቼ፣ ጎረቤት ቲቪ እያየሁ እኖራለሁ፡፡ ለነገሩ የተከራየሁት ክፍል ብቻም ሳይኾን እውቀቴም አነስተኛ ነው፤ በግሌ ለዩነቨርሲቲ መምህርነት የሚያበቃ ዝግጅትም ኾነ ክምችት ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ትችላለህ ካለኝ ግን ምን አደርገዋለሁ፡፡ ለምን መንግሥትን “ዋሾ” አስብላለሁ፡፡ ትችላለህ ካለኝ እችላለሁ፡፡ እኔ ከመንግሥቴ በላይ ስለ’ኔ ካወቅኩ ቡዳ ነኝ ማለት ነው፡፡

የገጠር የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ በመኾኔ ብቻ ሰዎች ትልልቅ ጉዳዮችን ያማክሩኛል። እናቴ ሲያማት ሐኪም ቤት ሄዳ ላልተፈለገ ወጪ መዳረግ አትወድም፡፡ የተማረ ልጅ አለኝ እያለች ሰፈራችን አቅራቢያ በሚገኝ “ኪዮክስ” እየሄደች “ሚስኮል” ታደርግልኛለች፡፡ ለእርሷ እኔ ዶክተርም ጭምር ነኝ፡፡ እስካሁን ያልተገለጠላት ነገር ቢኖር ለምን በየወሩ ብዙ ብር እንደማልክላት ነው፡፡ ለምን ትልቅ ቤት እንደማልገዛላትም በደንብ አልገባትም፡፡ ግን ተስፋ ታደርጋለች፡፡ በእውነት እላችኋለሁ እንኳን ቤት ባለቆቡን ሚስማር ልገዛላት አልችልም፡፡ ለእማዬ ግን ይህን ማስረዳት ቅስሟን መስበር ነው፡፡

አሁን አሁን ዩኒቨርሲቲ ማስተማሬን ተከትሎ ሰዎች በተዘዋዋሪ በሚያሳዩኝ አክብሮት እጅግ እየተሰቃየሁኝ እገኛለሁ፡፡ ቢያንስ ክብሬን የሚስተካከል ብር ሊኖረኝ ይገባል ስል አስባለሁ፡፡ በዚህ ረገድ መንግሥትን ተቀይሜዋለሁ፡፡ ደመወዝ እጨምራለሁ እያለ ሲያወራና ሲያስወራ ይኸው ስንት ዘመኑ፡፡

አብረውኝ ከሚያስተምሩ መምህራን ጋራ በትርፍ ሰዓታችን ስለ ደመወዝ ጭማሪ ማውራት አይታክተንም፡፡ ሁለት ዓመት ሙሉ እንዴት ሰው ስለደሞዝ ጭማሪ ብቻ ያወራል? ወሬውን ማን እንደፈጠረው አላውቅም፡፡ ሆኖም ከአጎራባች ዩኒቨርስቲዎች እንደተሰማ እገምታለሁ፡፡ ወይም ደግሞ ለማስተርስ ትምህርት አዲስ አበባ ሄደው የተመለሱ መምህራን ወሬውን ከዲግሪያቸው ጋራ ይዘውት መጥተው ሊኾን ይችላል የሚል መላምት አለ፡፡

ምንም ይኹን ምን እንዴት ለሁለት ዓመት ሰው አንድ ወሬ ያመነዥካል? ደመወዝ ጭማሪ፤ ደመወዝ ጭማሪ፣ ደመወዝ ጭማሪ. . .፡፡ አንድ ወቅት ሁላችንም ተሰላችተን ይህን ጉዳይ ላናነሳ ተማምለን ነበር፡፡ አዲስ የተቀጠረ አንድ “ጥላቢስ” የኾነ አስተማሪ “ጓደኛዬ ጋዜጣ ላይ ደመወዝ እንደሚጨመር አነበበ” ብሎ በማውራቱ የደመወዝ ወሬ በዩኒቨርሲቲው ዳግም አገረሸ፡፡ ጋዜጣውን አነበበ የተባለውን ልጅ ስልክ እንዲሰጠን ተማጸንነው፡፡ በጄ አላለም፡፡ “ላውድስፒከር” አድርጎ ራሱ ጓደኛውን እንዲያወራው ለመንነው፡፡ በሰበብ ላይ ሰበብ እያበዛ ነገ ዛሬ እያለ አሸን፡፡ በዚሁ ተናደን አገለልነው፡፡ ሲያንሰው ነው፤ በሰው ሕይወት ይቀልዳል እንዴ፡፡ ገጠር ውስጥ ማግለልን የመሰለ ቅጣት አይገኝም፡፡

ሐሳብ ተከሰተ

ሰሞኑን ባልተለመደ ኹኔታ የምኖረው ኑሮ እጅግ መረረኝ፤ አንገሸገሸኝ፡፡ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ ኾኖም እንደ ድንገት ድንቅ ሐሳብ ተከሰተልኝ፡፡ ዲቪ መሙላት፡፡ ቢንጎ!! ይህ ሐሳብ ለምን እስከዛሬ እንዳልተከሰተልኝ ገረመኝ፡፡ ያን ቀን ምሽት ደስ ብሎኝ አመሸሁ፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ የገጠር ሕይወቴ በተስፋ ተሞላች፡፡ ሌሊቱን ደስ ደስ የሚሉ ህልሞችን አየሁ፡፡ በተከታታይ ያየኋቸው ህልሞች መቼታቸው ሁሉ በአሜሪካ ከተሞች ላይ ኾነ፡፡

በነጋታው ጠዋት ስነቃ ግን ሞራሌና ወኔዬ ከዳኝ፡፡ እንዴት ዲቪ እሞላለሁ፡፡ የት ሄጄ እሞላለሁ፡፡ ሰው ቢያየኝስ፡፡ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እንደ ተራ ሰው ዲቪ ይሞላል እንዴ!

በመሠረቱ ዲቪ ከእኔ ስብእና ጋራ በፍፁም አይሄድም፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ መለመንና የሰው መመኘት አልወድም፡፡ እናቴ እንጀራ ከጎረቤት ተበድረህ ይዘህ ና ስትለኝ እንኳ በጀ ብያት አላውቅም፡፡ ጦሜን ማደር እመርጣለሁ፡፡ ትምህርት ቤትም ቢኾን ላጲስ ተውሼ አላውቅም፡፡ የተሳሳትኩትን ጽሑፍ በምራቄ አክኬ ፈትጌ አጠፋለሁ፡፡ እከካም ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ግን እውነቱ ይኸው ነው፡፡ ሁለተኛ ክፍል አብረውኝ ይቀመጡ የነበሩ ልጆችን መቅረጫ ብያቸው አላውቅም፡፡ እርሳሴን ከግድግዳ ጋር እያፋጨሁ አሾላለሁ፤ እቀርጻለሁ፡፡አሁንም እከካም ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ግን እውነታው ይኸው ነው፡፡

ዲቪ አገርህን ትተህ የሰው አገር አኑሩኝ እያልክ የምትለማመጥበት ሕጋዊ ማመልከቻ ነው፡፡ ይህን ማመልከቻ ሞላሁ ማለት የአሜሪካ መንግሥትን ተንበርክኬ ውለታ ዋልልኝ እያልኩት ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ፍፁም ከኔ አፈጣጠር እና ስብዕና ጋራ አብሮ የሚሄድ አይደለም፡፡ የአሜሪካ መንግሥትን በማመልከቻ ከምለምን በእግር ወደ አሜሪካ ብሄድ ይቀለኛል፡፡ የዲቪ መሙላት ሐሳብ ውስጤ ላይ ከፍተኛ መናወጥን ሊያስከትል የቻለው በዚህ የተነሳ ነው፡፡ ራሴን የከዳሁት ያህል ተሰማኝ፡፡

የተፈጠረብኝን ድብታና የስሜት መላሸቅ ለማስታገስ የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ሄድኩኝ፡፡ የዲቪ ወሬን እንዴት ብዬ እንደማነሳባቸው እያውጠነጠንኩ፡፡ ቀድሜ ጉዳዩን እኔው ካነሳሁት “አጅሬው! ዲቪ ሞላሽ እንዴ” እያሉ ዓመቱን ሙሉ መዘባበቻ ሊያደርጉኝ ይችላሉ፡፡ በዘዴ ነገሩን ማንሳት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ዘወትር የምንጎለትበት ቦታ ደረስኩ፡፡ ሁሉንም እዚያው ተሰብስበው አገኘኋቸው፡፡ ያው እንደተለመደው የደሞዝ ጭማሪን ጉዳይ እያመነዠኩ ነበር፡፡ ጋሽ ግርማ ወ/ጊየርጊስ በፓርላማ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ የደሞዝ ጭማሪ ጉዳይን አንስተዋል የሚል አዲስ መረጃ በመሰማቱ የሁሉም ፊት ፈካ ፈካ እንዳለ ለማስተዋል ቻልኩ፡፡ ኾኖም ጭማሪው ለዩነቨርሲቲ መምህራን ብቻ ሳይኾን ለሁሉም የኢትዮጵያ ሠራተኛ መኾኑ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አንዳንድ ሂሳብ-ዘመም መምህራን ለጉባዔው ለማስረዳት ሞከሩ፡፡ በደስታችን ላይ ዉኃ ቸለሱበት፡፡ የደሞዝ ጭማሪው ወሬ እየበረደ ሲመጣ የዲቪውን ጉዳይ ለኮስ ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡

“አናንተ! የዘንድሮ ተማሪዎች ደግሞ ጭራሽ የእንግሊዝኛ ፊደል ሳይጨርሱ ነው እንዴ ዩኒቨርስቲ የላኳቸው?” አልኩ ድምፄን ጎላ አድርጌ፡፡ ቀጥል የሚል ምልክት ተሰጠኝ፡፡ አንዱ ስሙን ሲጽፍ አይቼው በጭራሽ “ቫውል” አይጠቀምም፤ ታምናላችሁ? ስሙ ተሻለ ነው፡፡ እንዴት “ስፔል” እንዳደረገ ታውቃለህ “ቲ፣ኤስ፣ኤች፣ኤል”፡፡ ባወራሁት ነገር ማንም አልተገረመም፡፡ ይልቁንም ሁሉም ከዚህ የባሰ የሚሉትን እያነሱ ማስረዳት ጀመሩ፡፡ አሁን ወደ ዲቪው ጉዳይ መግቢያ ሰዓት እንደኾነ ተሰማኝ፡፡ የ“ስፔሊንጓን” ወሬ ኾነ ብዬ እንጀመርኳት አልገባቸውም፡፡

“ስሙኝማ! ከተማ ትናንት ተለጥፎ ያየሁትን ልንገራችሁ፡፡ ዲቪ እንሞላለን የሚለው ጽሑፍ ላይ “Good Luck” የሚለውን ቃል እንዴት ጽፈውት ዐየሁ መሰላችሁ፣ “Good Lack”፡፡” ከገመትኩት በላይ ሳቁልኝ፡፡ ሳቃቸው እንደበረደ ከመሐላችን አንዱ “ዲቪ ተጀመረ እንዴ?” ሲል ጠየቀ፡፡ በቀጥታ ሊመልስለት የደፈረ ግን አልነበረም፡፡ ቀለል አድርገው፣ “እኔንጃ”፣ “መሰለኝ”፣ “ኸረ!”፣ “ይባላል” አሉ፤ የተወሰኑት፡፡

አውቀው ነው፡፡ ሁሉም መቼ እንደተጀመረ አይደለም ስንት ሰዓት ላይ እንደተጀመረ ያውቃሉ፡፡ ዲቪ ሞላ ላለመባል ነው፡፡ ተነቃቅተናል፡፡

DV regardless of CV

ያለንባት ከተማ በኦባማ ፎቶዎች ከተጥለቀለቀች ሁለት ሳምንታት አልፈዋታል፡፡ ዲቪ እንሞላለን የሚሉ ማስታወቂያዎች የትም ነው የተሰቀሉት፡፡ ከሁሉም የገረመኝ ግን ይህን ማስታወቂያ ዩኒቨርስቲያችን ውስጥ በትልቅ ባነር ተሰቅሎ ማየቴ ነው፡፡ የተማሪዎች ካውንስል በቅናሽ ዋጋ ዲቪ መሙላት በመጀመሩ የካፌ ሰልፍን የሚያስንቅ ረዣዥም ሰልፎች በዩኒቨርስቲው ተፈጥረዋል፡፡ ዲቪ ለመሙላት ረዥም ሰልፍ፡፡ ልክ አዲሳባ ኢሚግሬሽን ጠዋት ጠዋት አየው የነበረውን ሰልፍ አስታወሰኝ፡፡ ይህን ያየሁ ቀን ከፍተኛ ድንጋጤም ከፍተኛ ግርምትም ተፈጠረብኝ፡፡

ነገሩ ስላስደነቀኝ ተጨማሪ ነገር ለማግኘት በዩኒቨርስቲው ግቢ መዘዋወር ጀመርኩ፡፡ የዲቪ ማስታወቂያዎች በተማሪዎች ካፌ፣ በመማርያ ክፍሎች ደጅ ባሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ በቤተ መጻሕፍቱ በር ላይ ወዘተ ተለጣጥፎ አየሁ፡፡ የማስታወቂያው ይዘት ተማሪዎች ዕድሉ እንዳያመልጣቸው እና እንዲጠቀሙበት የሚያባብል ነው፡፡ የተማሪዎች ካውንስል ነው ይህንን የሚስተባብረው፡፡ በኔ ጊዜ የነበረው የተማሪዎች ካውንስል የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ ያስተባብር እንደነበር ትዝ አለኝ፡፡

ወደራሴ ጉዳይ ተመለስኩ፡፡ በእርግጥ አሳፋሪ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሳያውቅ ዲቪ መሙላት አለብኝ፡፡ እንዴት? በትንሽ ከተማ ውስጥ እንኳን እኔ ያለሰፈሯ የመጣች ዝንብ እንኳ ትታወቃለች፡፡ ለማንኛውም አማራጮችን ለማየት ከዩኒቨርሲቲው ወደ መሀል ከተማ የሚወስድ ታክሲ ለመያዝ ተንቀሳቀስኩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ዋና በር ላይ ታክሲው እስኪሞላ ብዙ ነገር ለመታዘብ ቻልኩ፡፡ ቀድሞ የተማሪ “ሃንድአውት” በማባዛት ይጠመዱ የነበሩ ፎቶኮፒ ቤቶች መስኮቶቻቸው በዲቪ ማስታወቂያ አሸብርቋል፡፡ እዚህም ዲቪ ለመሙላት ብዙ ተማሪዎች ተሰልፈዋል፡፡ በእጆቻቸው የሚባዙ ሃንድ አውቶች ሳይኾን የዲቪ ፎርሞችን ነበር የያዙት፡፡

ከተማ ደርሼ ከታክሲው እንደወርድኩ ወደ አንድ ኢንተርኔት ካፌ ጎራ አልኩኝ፡፡ ከተደረደሩት ኮምፒውተሮች ወደ አንዱ ጠጋ ብዬ ኢንተርኔት የምበረብር መስዬ የቤቱን ደንበኞች መበርበር ጀመርኩ፡፡ ሰዎች ነጭ አቡጀዲ እየተደገፉ በወረፋ ፎቶ “ቀጭ” ይደረጋሉ፡፡ ብዙ ወጣቶች፣ ጥቂት ጎልማሶች፣ ጥቂት ትልልቅ ሰዎች፣ ባልና ሚስት፣ ባል ሚስት እና ሰባት ልጆቻቸው፣ ጋዝ ልትገዛ የተላከች የቤት ሰራተኛ፣ መካኒክ ከነሽርጡ፣ ያስተማርኳቸው ተማሪዎች ወዘተ፣ ቤቱ የማያስተናግደው ዐይነት ሰው የለም፡፡ ሁሉም ለዲቪ የጭንቅ አማላጇን ስም ይጠራል፡፡ ይህ ሕዝብ አገሪቱን አይፈልጋትም እንዴ፡፡ ለምን አንድነቱን በግልፅ ጨረታ ሽጧት አይሄድም?

በዚህ ኢንተርኔት ቤት ጠረጴዛ ላይ ዲቪ የተሞላበት ወረቀት ተከምሯል፡፡ በአመቱ መጨረሻ የማርማቸውን የተማሪዎቼን ፈተና ወረቀቶች አስታወሰኝ፡፡ ለነገሩ የዚህን ዘመን ተማሪዎች ፈተና ከማረም የሰሊጥ እርሻ ማረም ይሻላል፡፡ ወይም ደግሞ ይህንን የዲቪ ክምር ማረም ሳይሻል አይቀርም፡፡ ሁለቱም ‹‹ስቤሊንግ›› ማረም ስለሆነ ብዙም አይራራቁም፡፡ የአሜሪካ መንግስት ዲቪ አራሚ አድርጎ ቢቀጥረኝስ ብዬ አሰብኩ፤ ለአፍታ፡፡ ሐሳቤ በራሱ ፈገግ አሰኘኝ፡፡ አይ አሜሪካ ስላንቺ ማሰብ በራሱ ፈገግታን ይፈጥራል ለካ፡፡

በዚህ ኢንተርኔት ካፌ ብዙ ሰው ዲቪ ለመሙላት የሚሽቀዳደመው ከዚህ ቀደም በዚህ ቤት ዲቪ የሞሉ አራት የከተማዋ ነዋሪዎች ዲቪ ደርሷቸዋል በመባሉ ነው፡፡ ገድ አለው ይባላል ይህ ቤት፡፡

ወደራሴ ጉዳይ ልመለስ፡፡ ዘንድሮ እንዴትም ብዬ ዲቪ መሙላት እንዳለብኝ የተነጋገርን መሰለኝ፡፡ ስለዚህ እዚሁ ገድ አለው የሚባልለት ቤት ለምን አልሞላም፡፡ የማስተምራቸው ልጆችና የሚያውቀኝ ሰው በቤቱ አንደሌለ ሳረጋግጥ ፎቶ የምታነሳዋን ልጅ ዲቪ መሙላት ፈልጌ እንደመጣሁ ነገርኳት፤ የሞት ሞቴን፤ በሹክሹክታ፡፡

“ይቻላል፣ አስር ብር ከፍለህ ፎቶ ትነሳና ይህን ፎርም ሞልተህ ነገ ማረጋገጫ እንሰጥኻለን፡፡” አለችኝ ጮኽ ብላ፡፡አሳቀቀችኝ፤ምን አለ እኔ እንደማወራው ቀስ ብላ ብታወራ፡፡ ተማሪዎቼ እንዲሰሙ ነው? ምቀኛ!

እንደተረዳሁት ከሆነ የኢንተርኔት ፍጥነቱ ቀን ቀን ቀርፋፋ ስለሆነ ኢንተርኔት ቤቶቹ ዲቪ ፎርሙን በወረቀት ብቻ እያስሞሉ ሌሊት ሌሊት በኢንተርኔት ይልኩታል፡፡ በነጭ ወረቀት ለሞሉት ሰዎች በነጋታው የማረጋገጫ ደብዳቤ ይታደላቸዋል፡፡ በዚህ መሀል የስም ስህተት ቢከሰት ግን ማን ተጠያቂ እንደሚሆን አልገባኝም፡፡ እድሌን ማበላሸት የለብኝም፡፡ “እመለሳለሁ” አልኩና ሹልክ ብዬ ወጣሁ፡፡

በከተማዋ ያሉ ሁሉም ኢንተርኔት ቤቶች ደንበኞቹ እያዩ ዲቪ እንደማይልኩ ተረዳሁ፡፡ ይህ መልካም ነገር አይደለም፡፡ ስለዚህ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረብኝ፡፡ በከተማዋ ወደሚገኘው አንድዬ ፖስታ ቤት አመራሁ፡፡ በሩ ላይ ከፍተኛ መጨናነቅና ፀብ የሚመስል ግርግር አየሁ፡፡ በቅርቤ ያገኘኃትን የገጠር ልጅ ስለጉዳዩ ጠየቅኳት፡፡ ዲቪ ለመሙላት ጠዋት ወረፋ የያዙ ሰዎች ጎረምሶች ያለወረፋቸው እየገቡ አስቸግረዋቸው ረብሻ እንደተፈጠረ ነገረችኝ፡፡ የፖስታ ቤቱ ሰራተኞች ደግሞ በስነስርዓት ወረፋ ካልተያዘ አናስተናግድም ብለው ማመፃቸውን ጨምራ አብራራችልኝ፡፡

ፖስታ ቤት በር ላይ ያሉትን ማስታወቅያዎች ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ ዲቪ ዘንድሮ ለአንድ ወር ብቻ እንደሚቆይ፣ የቀሩት ቀናት ጥቂት እንደሆኑ፣ ዲቪ በፖስታ ቤት መሙላት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት፣ ለምሳሌ ዲቪው ሲመጣ የስም ስህተት ቢኖረው ፖስታ ቤት ለአሜሪካ ኤምባሲ ቀጭን ደብዳቤ የመፃፍ ብቸኛ ባለመብት እንደሆነ ወዘተ ይናዘዛል፡፡ፖስታ ቤት መንግስታዊ ድርጅት ነው፡፡ ዜጎቹን በተዘዋዋሪ ሌላ አገር እንዲሄዱ ተግቶ እየሰራ እንደሆነ ነቃሁበት፡፡

ለነገሩ እኔ ብቻ ሳልሆን የመንግስት ባለስልጣናትም ዲቪ ይሞላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ዲቪ ደርሷቸው ቀስ ብለው ሊሄዱ ሲሉ አይደል እንዴ የተደረሰባቸው፡፡ እኔ የምሰራበት ዩኒቨርሲቲ የ‹‹ሪሰርች›› ፕሬዝዳንትም ሰሞኑን ዲቪ ሲሞሉ እንደታዩ በወሬ ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ ሰውየው እድሜያቸው ገፍቷል እኮ፡፡በዚያ ላይ አሜሪካ ነው የተማሩት ሲባል ነበር፡፡ ተንቀዥቅዠው መጥተው ነው ጉድ የሆኑት ማለት ነው፡፡ ዲቪ ሲቪ እንደማይመርጥ ተረዳሁ፡፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዲቪ መሙላት ይፈልጋል፡፡ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሚባለው ውስጥ ደግሞ እኔ እገኛለሁ፡፡ ስለዚህ ዲቪ እሞላለሁ፡፡ ቅድም ወደነበርኩነት ኢንተርኔት ካፌ ሄድኩኝ፡፡ ፈገግ ብዬ ፎቶ ተነሳሁ፡፡ኮስተር ብዬ ፎርሙን ሞላሁ፡፡ ከኢንተርኔት ቤቱ ስወጣ ከሸሌ ጋር ያደርኩ ያህል ቀፋፊ ስሜት ተሰማኝ፡፡ አገሬ ኢትዮጵያ ሆይ አንቺም ዲቪ ሞልተሸ ብትሄጂ ይሻልሻል አልኩ በሆዴ፡፡

Twitter Digg Delicious Stumbleupon Technorati Facebook Email

46 Responses to “ዲቪ እና CV”

 1. enquan dv molah… i was a ‘university’ teacher like …. i was among the lucky to win the lottery. there is no shame in leaving ethiopia. here there is freedom. if you are a harder worker. you will reap the benefit. Though you will be a janitor for a few years, life here is better than being a university lecturer in a country jailed by woyanie.
  if you got heart, struggle for change, if heartless like me better to leave the country.

 2. I like it!—What always surprises me has been stated here— The commitment of the Ethiopian postal service to serve the community..lol

 3. ታሪኩ አሳዘነኝ፣ የጸሐፊው የጽሑፍ ችሎታ አስደነቀኝ አሳቀኝም። መድኃኔዓለም ሃሳብክን ያሳካልህ አቦ!

 4. NICE FICTION!

 5. bearifu bzu topic dasehal.enamesegnalen,zendro yemiyasfelegew ende teshale aynetu new siyanebu degmo ende kedamawit azeb

 6. What a depressing fiction!! Whoever you are,dont rub off your pessimism on others.
  My remedy would be to read Mohammed Selman’s great piece soon.

 7. ልብ ወለድ ሆነ እውነተኛ ታሪክ ያለው እውነታ እንደሆነ ይሄው ነው እድሉን ቢያገኝ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ
  አገሩን ለቆ እንደሚወጣ የታወቀ ነው እድሜ ለልማቱ መንግስታችን ወያኔ

 8. I wish i could meet the writer. he is so good. One thing i noticed, he better be a journalist than a lecturer or anything else. And no matter what, there is no place like home!! Am counting down the day am gettin back to mother land, ETHIOPIA apart from all the political situations.

 9. Lovely story!! DV never be the solution.You might enjoy some material wealth… But weather you like or not you suffer from lack of morals and Passion to your home land! If this is something you can afford,DV is the easy way out!!

 10. This is not a fiction. i am one of them who is out for timirt out of the country i was teaching in. I have no interest to get back home. tselote hulu mnew yehone neger begetemegn ena bekerehu.

 11. I read this from America- for me it is a tragedy- the author had the same back ground as mine except for he doesnt borrow pencil or any thing- ethiopian for real. He was that guregna being a kid- now a grown up honest person proud of himself but not his country any more-same as i was- our difference: am here on a scholarship paid by the university I study at. Hey, Mr. author- come here- but please email to me at walarguuf@yahoo.com – we will do something for the country that gave us the best it had- mind you many of your friends dont have the income u get. But you have the aspiration for more: thas great. So come soon.

 12. I read this from America- for me it is a tragedy- the author had the same back ground as mine except for he doesnt borrow pencil or any thing- ethiopian for real. He was that guregna being a kid- now a grown up honest person proud of himself but not his country any more-same as i was- our difference: am here on a scholarship paid by the university I study at. Hey, Mr. author- come here- but please email to me at walarguuf@yahoo.com – we will do something for the country that gave us the best it had- mind you many of your friends dont have the income u get. But you have the aspiration for more: thas great. So come soon.

 13. ጽሁፉን ወደድኩት ከኔ ጋር ተመሳሳይ ስሜት ተጋርተናል:: የኔን ጽሁፍ እዚህ ማግኘት ይቻላል http://www.facebook.com/note.php?note_id=443911451723

 14. I really like this article. It has so many interesting things in it. The guy seems to be talking about DV but he is giving us a brief summary of of the current political, economic and social situation of the country. Really is there a better way than writing such satirical piece which shows you how the education system is deteriorating, what the ambition of the young generation is, how government seems not to care at all about the fate of its citizens and how desperate the majority of Ethiopians are. This is art at its best and I want to again appreciate the writer.

 15. the writer is simply rubbish.There are so many things that he wants to know.That the salary is poor.teachers’ knowledge is minimal,etc.

  The main problem of all our people is ignorance.people write before they learn.He doesn’t have the slightest knowledge about the country and the people.He doesn’t have the slightest courage and nationalism to change things here for the people.Go write you rubbish.
  before trying to change people,you better change yourself.

 16. I do not understand why the Ethiopian government doesn’t care if the people of Ethiopia leave their home land and move to US or any country. What country do you know that helps its citizen to apply for immigrant case like Ethiopia……for me there is no one……….Ethiopia…I’m crying for you………..

 17. Aron Tsehaye, good job!

 18. THE Writer is so politically motivated. if you read between the lines, it is very very dangerous. Hmmmm

  However, he can write. No question.

  • heny ersu endfechiew yileyayal.Amrgna eko new!!! ant keflek befkedkew menged mendat becha new.ayi heni!!!!

 19. Amazing writer. His way of writing and especially the way he revealed reality with artistic quality forced me to stay focus on the it.
  I wish you good luck not “lack” bro.

 20. A great writer. It is political satire at its best.I couldn’t help laughing as I go through the article. Aaron did a far deeper and more penetrating analysis of the sad realities behind DV application in such a short piece than what some could do in a book.He should be applauded for the job well done.

 21. TO THE AUTHOR:
  I commend your writing skills minus some of the exaggerations.While, I agree with your portrayal of the Ethiopian mindset, especially among the young, it is very sad to see you leaning to join the flock too, apparently for the wrong reason.

  Pardon me if I sound judgmental. But I had been in your shoe (teaching at what you call “Geter” university)for a third of your salary today.First, there is nothing wrong with teaching at the “Geter” university and in fact its an opportunity if you open your eyes, as it had been for me and most of my friends. Second, it is so troubling to read you saying you quit reading.How come you “eat enough” to joke around with your friends but you “cant eat enough” to read? That is really a dull point and I really hope that was one of your blunt exaggerations or else its a career suicide, whether you are teaching or not. Third, if your desperation has its roots in not being able to make money while in a state university, you are barking on the wrong tree pal. With money in mind, may be DV is not a bad choice and best of wishes.

  But if you were at all any serious about a future as an academician, with the right attitude and some little effort, your chances of crossing the borders with dignity(which appears to be of great importance to you) are much higher at the university than with the DV.

 22. What an epic story!! A Beutifully layered and artistically presented agony of beeing a lecturer in Ethiopia. I share the same story- a lecturer now pursuing further study abroad, and this writer makes me to re-think my return home ….በዚያ ላይ አሜሪካ ነው የተማሩት ሲባል ነበር፡፡ ተንቀዥቅዠው መጥተው ነው ጉድ የሆኑት ማለት ነው፡፡
  Gush, not me

 23. የሞትንም እኛ 30 October 2010 at 3:08 am

  የስድሳዎቹ ትውልዶች ተማሩ ተብለው ተላኩ፤ እውቀት በገበዩ ቁጥር አገራቸውን እና ንጉሳቸውን የማይከዱ ነበሩ እና ተመለሱ፤ እነሱው መልሰው ጥያቄ አመጡ፤ ለውጥ ያስፈልጋል አሉ፤ ለውጡን በየትምርህርት ቤቱ እንዲስፋፋ የማድረግ ዕድል ነበራቸው። ተማሪዎቹን አትንኩዋቸው የሚሉ ንጉስ ነበራቸዋ! ይሳሱላቸው ነበር። ንጉሱ ከእነ ድካማቸው በተማሪዎች ላይ የሚጨክን አንጀት አልነበራቸውም። ለ…ውጥ ፈላጊዎቹ ግን ሥልጣን ላይ ለመውጣት ተረባረቡ፤ በጫካ እና በከተማ ተራወጡ። የከተማዎቹ ገዙ፤ ተገለበጡ፤ ለተማሪዎች እና ለለውጥ ፈላጊዎች ግን ርህራሄ አልነበራቸውም። ከተማሪነት ወደ ወደ ጫካ የሄዱት መጡ ኢትዮጵያ እጃቸው ላይ ወደቀች፤ ለእነርሱ ርህራሄ የነበራቸው ንጉሱ ትዝ አላሉዋቸውም፤ የሚቀናነቀናቸውን ሁሉ ጠርገው አጠፉ፤ ትዝ ይሏችሁዋል 42ቱ ስንት ሀብት እና ንብረት የፈሰሰባቸው ምሁራን? የአዲሶቹን ገዢዎች ሓሳብ ከማይቀበል ይልቅ የሚባረር ለኢትዮጵያ መድህን ነው ብለው አወጁ፤ የኢትዮጵያን ተስፋ አጨለሙት።

  እየገደሉ እያስገደሉ መጥተዋልና ለወንድማቸውም እንኳ የሚራራ አንጀት አልፈጠረባቸውም። አገሬውን ሁሉ አገሩን የሚወድ ሳይሆን አገሬ ምን አደረገችልን ብሎ መሮት ሌላ አገር ናፋቂ አደረጉት። ዲቪ ነገሰ፤ በሰው ልብ ውስጥ እንደ ጽላት ሆኖ አደረ። አገሩን የሚወድ ትውልድ ለማፍራት እንዳይችል የሚያደርገው የመለስ አገዛዝ ሰውን ሁሉ የዲቪ ሰለባ አደረገው፡፤ ከተሰራበት እና ፈቀቅ ሊል ከማይችለበት ማንነት ፤ እናቱ እንጀራ ተበድረህ ና ሲሉት ከመበደር ይልቅ ጦም ማደር ይመርጥ የነበረውን ሰው ውጭ አገር አስናፈቁት፤ አስፈገጉት፤ ከራሱ ጋራ ሙግት እንዲገጥም አደረጉት። ለእኔ ይኼ ታሪክ ከልብ ወዳዊ ይዘቱ ይልቅ እየፈረሰ ያለውን የኢትዮጵያዊ ማንነት መገንደስ በግልጥ ያሳየኛል። ከአገሩ የወጣ አገሩ እስኪመለስ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ የሚለውን የዳያስፖራ ህይወት ምንነት በደንቡ ሳያውቀው እንዲናፍቀው ተደርጓልና። ይናፍቀዋል። የውጡት ግን የመመለሻውን ቀዳዳ ይናፍቃሉ።

  ውድ የፌስ ቡክ ወዳጆች፤ መለስ የያዘው የሥልጣን ሱስ አናቱ ላይ ቢወጣበት ያመጣው መዘዝ እስከምን ድርስ እንደተጓዘ ልብ ብላችሁዋል። አሁን ባለጌ እንዳትሉኝ እንጂ መለስ በእውነተኛው የወሲብ ዓለም የተዋጣለት መሆን ስላቃተው (አዜብን መብ . . ስላልቻለ) የውሲብ ስሜቱን እየተወጣ ያለው በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ነው። ሁላችንም ተበድ. . . ናል። ዛሬ አይናችን ካልተከፈተ መቼ ነው ከዚህ የምንወጣው? ? ? ?

  • This piece is too vulgar. I thought AN is a moderated forum and if that’s the case how do you allow such irresponsibly vulgar comments in your forum. Its one thing to express your opinion and dissatisfaction but it is completely different to insult people (whoever they are) such things should never be tolerated. I hope the site moderators will take note and remove it immediately.
   For the record I am not a government supporter and neither am I an opposition member. I am just a citizen concerned about my country.

  • Dear የሞትንም እኛ
   Hey, I love your comment man. You too have excellent writting skill. Please, keep on writing and let’s know where to find your comments and literary works. Thanks

 24. Literature is the beauty of life, it is a face miror reflecting to one’s life teaching others for more exploration and discovery through the venture of life.

  The author of this piece is a skilled writer who has cuptured my mind throgh simple but complex personal view in a satiric pun. Eventhough the setting of the story is fictional Geter,it has penetrated the mind of DC resident who toils to endure the hardship of two or three jobs for living.

  You need to imagine that who would have luxury of time to read books and norish the thirust of knowledge. That is life in America. I uphold you as a true and honest citizen of my mother land. I am praying hard that almighty God to give me a chance to go back home and share at least a little of what I have before I expire from this world. May god bless you and if you want, please send me a message on this e-mail and we will talk more. May God bless you and I respect you and honor you for your literary view. I am proud of you.Your political view is incapsulated that dum Meles would not understand the message.

 25. እጅግ ድንቅ ጽሁፍ፡ ኣንዳንዶቻችን ልብወለድ ስንለው ያየሁ መሰልኝ? መቼ ይሆን እውነት በጥሩ ብዕር ስትሟሽ የገለፀችውን ሀቅ ትተን ልቦለዳዊ ስም ሰጥተናት የምናልፈው?
  ፖስታ ቤትን ሰልፍ ካጨናነቁት ውስጥ አንዱ ነኝ።

 26. በጣም መሳጭ ጽሁፍ ናት::እኔም የገጠር ቴክኒክ ት/ቤት አስተማሪ ነበርኩ
  ለዛውም ‘ጋሼ’ እየተባልኩ የምጠራ የነበርኩ አንድ አመት እንዳስተማርኩ በ dv ከአገር እመለጥኩ በ2008,,,በቅርቡ ለናቴ ቤት ገዝቼ ከኪራይ ቤት ኑሮ ግላግያት ምርቃት በምርቃት ሆኛለሁ.እንደውም ጎረቤት ለቡና ሲጠራ በትልቁ የተሰቀለውን የኔን ፎቶ እያዩ ስለኔ ለጋስነት ነው የቡና ወሬው ማሳረጊያውም እኔን መርቀው ልጅ ያላቸው ልጃቸው የእኔ እድል(DV) ና ለጋስነት እ/ር እንዲሰጠው መርቀው ተመራርቀው ይጨርሳሉ

 27. its all true I used to run internet cafee business in ethiopia and each year this time it was good for my business, b/c it was like evrybody regardless of his educational or age background wants to leave the country, so it was hot for the business,but bad for the country, it seems like no one wants to live in ethiopia, i am very sorry about it, it shows how life is hard in ethiopia its not that we ethioopians hate our country its the life condition that forces us to leave the country. we miss our country from where we are but how can we tolerate weyane and his racial dictatorship after we saw what democracy is.. poor ethiopia

 28. matt. why do you so upset? agames eat with out limite , dance day and night and again they want all other ethiopians cover their crimes . You are ripping our country,

 29. It was a nice read. I think the writer has depicted what most Ethiopians go through on a daily basis. I used to be a government employee. I loved what I did, though I didn’t get along with the government and its third-rate suppporters. I came to the US to do my masters. During my stay in the US, what I have learned is that what most Ethiopians who come to the US get is material solace – nothing less, nothing more. And even that material stuff is minimal by the standard of America. I have now decided to get back to Addis, and I can’t wait to get there. I’d rather go hangry and do something substantive in my country than be a runner-boy of something in the US living a relatively better life (and that only with respect to the material side of life). But I understand what others go through, and respect what they decide to do.

 30. Hey Kuku, Ofcourse you are Kuku of the Wayane. Did you understand what the guy even said on his writing. Is it a shame to be poor. When you said you were not like him as a kid. Bravo you were a rich peoples’ kid. Shame, sahme hide your self and study english to be able to write better.”university student’ By the way he loves his country that is why he wrote what he wrote. If you understand literature.

 31. I always thank God the day I left Ethiopia, to be honest. What did I get after post-high school studying of about 8 years? Struggling to survive. When I was in Ethiopia, I would aspire one day I would be better off as a result of hard work and studying. After working over nine years I din’t have the money to buy even a condominium. So, I dicided to leave Ethiopia. It doesn’t mean I hate Ethiopia. But life is really difficult. When I talk to my freinds I feel so sad. Specially now a days life is challenging.
  I am better off now and Hopefully I will have what I aspire to get. I am sure one day I will go home for good.

 32. i have the same history with U. And i wish U proud of god with U!!!!

 33. hey, R u fikir yilikal of etv? i am a great fun of you. we are namesakes. i really need to know you closer.

  Addisnegers where is the next chapter of this piece?

 34. To the author.
  wendime tsihufihin betam wedijewalehu.neger gin america meto dihinetin lemashenenef memoker wirdet aymeslegnim.ke college behuala yeneberegn ye ethiopia hiwot ejig askeyami neber.ke dihinetu betam yekefaw ye poletica witiretu ena netsanet matatu neber.america metiche gin betesfa yetemola hiwot menor chiyalehu.ewnet lemenager dehinetu lekefabet ena netsanetun lata sew america betam tiru amarach nech.thanks

 35. That is real life back home. it is all about choice, we need to admire his literature. We can’t put our selfs in to his shoe. I like his expression. Better way to return something we lost as Ethiopian is first we have to accept this is true and happen now. Even big guys want to leave the country. We missed one thing.

  O God I love if I live back home, but a lot things make u feel this is not like home, only home is feel Your if u are happy with family and stuff living with u. that is also rented ..Who is really happy with home and facility u live with…a lot of issue hope we can change that if we start to think back like this is your country and your home. As we observe from suggestion we don’t want to admit the problem we like to blame a person like there is some motive inside…guys God knows about that but we should acknowledge that problem is real and what we can do as a citizen to return back home…one thing all we live outside we can help to tell the truth how we live and how we work for living and how difficult every days is living in some ones country. So many of us have that false image like one my friend mention about buying house to his family can motivate millions how love their mothers to make them happy nothing is more important that this as a child but this all the bull shit drive nation to crazy and ignorance. I know how difficult life back home is leaders (religious or political or community) feel they are not representing you nobody is speaking truth , I can share there is a lot of reason behind for them too but still all of us the same goes to deep shit. Radio and TV also tells you same shit like feeling is there any other Ethiopian live or am I not living here. We all from top to bottom try to defense each other, protect our ego, arguing each other for nothing. My follow citizen we have a lot shit to avoid first and think about we can do better that today, God make as same as this people we admire here. I will start from myself I lost all my sense as follow Citizen. I don’t know why and where I got this but I have no ear to listen positively. But I feel we can change our self at list to the follow citizen specially who this day in University. We can back our self at list we pray for that, ( when I heard Ethiopia is growing this much and that much I feel yes may be right u can divide country wealth with people u have…I was there but I am not part of that number may the TV is transmitted to those I don’t know because at list I know all the truth happen every day and even happen to me but other peoples are arguing about. That is way I feel I lost something) prey to me and to those who lost the same as I lost….Hope we will get it back once we all believe on that is true image Ethiopia has today.

  I Wish I could have something better.

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.