ስለ እኛ
AddisNegeronline.com የአዲሰ ነገር ጋዜጣ ይፋዊ ድረ ገጽ ነው። አዲስ ነገር ጋዜጣ በጥቅምት 16 ቀን 2000 ዓ.ም መታተም የጀመረችና ለሁለት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየች ሳምንታዊ ጋዜጣ ነች። አዲስ ነገር በጋዜጣው መስራቾች እና ባልደረቦች ላይ ከመንግሥት በደረሰው ጫና እስከተዘጋችበት እስከ ታህሳስ 2002 ዓ.ም ድረስ ከፍተኛ ተነባቢነት ከነበራቸው የአገሪቱ ጋዜጦች ቀዳሚው ለመሆን በቅታ ነበር።
ጋዜጣዋ በወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሥን/ጥበብ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ትንተናዎችን በማቅረብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቀባይነትን ማግኘት ችላለች። በዚህም በምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ የመንግሥት እና የሌሎችም ድርጅቶች ባለሞያዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቛማት ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች ወዘተ ዘንድ ተነባቢ ለመሆን በቅታ ነበር።
ልክ እንደ ጋዜጣው ሁሉ በድረ ገጻችንም ለአገራችን ገንቢ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ በሚል እምነት ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡ አስተያየቶች፣ አቋሞች፣ ትንተናዎች፣ ዘገባዎች…ይቀርባሉ።

No comments yet... Be the first to leave a reply!